ፀደይ ባንክ በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

   IMG 20231203 183924 570

አዲስ አበባ: ኅዳር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፀደይ ባንክ በአማራ  ክልል በዋግኽምራ እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች  የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጎል። የባንኩ ዋና ፕሬዚዳንት መኮንን የለውምወሰን ድጋፉ በአመልድ ኢትዮጵያ በኩል ለተጎጂዎች አንዲደርስ አስረክበዋል።

የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር  ዓለማየሁ ዋሴ (ዶ.ር) ከ450 ሺህ በላይ አስቸኳይ የዕለት ምግብ የሚፈልጉ ወገኖች ስለመኖራቸው ጠቁመዋል። በፀደይ ባንክ በኩል የቀረበው ድጋፉም አስፈላጊ በመሆኑ ባንኩን አመስግነዋል።

ዶክተር ዓለማየሁ ሌሎች ባንኮች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ባለሃብቶችም ድጋፍ በማድረግ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ:- አሚኮ

Copyright © 2012 ORDA Ethiopia.
All Rights Reserved.