የተፈናቃዮች፣ ከስደት ተመላሾች እና የአካባቢው ማህበረሰቦች በራስ የመተማመን፣ የአካባቢ ውህደት እና ማህበራዊ ትስስርን ማጠንከር ፕሮጀክት
ፕሮጀክቱ በአማራ ክልል አዊ ዞን በጓንጓ፣ ጃዊ እና ፋግታ ለኮማ ወረዳዎች እና በቻግኒ ከተማ አስተዳደር እ.ኤ.አ ከ2021 እስከ ህዳር 2024 ከቢኤምዜድ/ ከጀርመን የኢኮኖሚ ትብብር ቢሮ/ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ እየተተገበረ ይገኛል፡፡
ከሰኔ 24/2015 እስከ መስከረም 30/2016 በፕሮጀክቱ የተከናወኑ ተግባራት በሂሳብ አያያዝ፣ በብድር አጠቃቀም እና የሥራ እቅዶች አወጣጥ እና ትግበራ ዙሪያ ለ347 ወጣቶች (ሴ፡199) ለሥራ ዝግጁ እንዲሆኑ ስልጠና ሰጥቷል፡፡ እንዲሁም ለ113 ወጣቶች (ሴ፡57) ለእያንዳንዳቸው 25ሺህ ብር በጥቅሉ ብር 2.8 ሚሊዮን የመቋቋሚያ የመነሻ ካፒታል ተሰጥቶቸዋል፡፡
በተጨማሪም 112 ወጣቶች (ሴ፡57) በዶሮ እና በበግ እርባታ፣በባልትና ዝግጀት፣ ካፊ እና ሱቅ ሥራዎች ዙሪያ ተሰማርተዋል፡፡ በተጨማሪም 9 ወጣቶች (ሴ፡5) በተለያዩ ተቋማት የሥራ እድል እንዲያገኙ እድሉ ተመቻችቶላቸዋል፡፡ 112 ወጣቶች (ሴ፡60) 75 ኢንተርፕራይዝ አቋቋመው ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ በሩብ አመቱ በ2.6 ሚሊዮን ብር ወጪ በአራት ወረዳዎች የወጣቶች አንድ ማዕከል አገልግሎት ግንባታ እና የቁሳቁስ ማሟላት ሥራ ተሠርቷል፡፡