በጦርነት ለተጎዱ ማህበረሰቦች የተቀናጀ አስቸኳይ የግብርና ድጋፍ ማድረግ ፕሮጀክት ለተጠቃሚዎች የማቋቋሚያ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡
በአመልድ ኢትዮጵያ በጦርነት የተጎዱ ማህበረሰቦች የተቀናጀ አስቸኳይ የግብርና ድጋፍ ማድረግ ፕሮጀክት በቬልት ሁንገር ህልፈ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል ሁለት ወረዳዎች ማለትም ደባርቅ እና ዳባት ወረዳዎች በጦርነት ንብረታቸው ለወደመባቸው 4 ቀበሌዎች እ.ኤ.አ ከመጋቢት 2023 እስከ የካቲት 2024 ድረስ ድጋፍ እያደረገ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ለ3,960 ተጠቃሚዎች (ሴ፤ 791፤ የአካል ጉዳተኞች 134) 790 ኩንታል የተሻሻለ የስንዴ እና ጤፍ ዘር ድጋፍ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም እንስሳቶቻቸው ለሞቱባቸው 271 አርሶ አደሮች (ሴ፡50፤ የአካል ጉዳተኞች፡ 16) 813 የእርባታ በግ እና ፍየሎች ድጋፍ እና 4,241 ኩንታል የተቀነባበረ የእንስሳት መኖ ለ672 ተጠቃሚዎች (ሴ፡92) ስርጭት ተደርጓል፡፡