Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች በአመልድ ኢትዮጵያ ትራኮማን የማስወገድ ፕሮጀክት አበረታች ስራዎች

በአመልድ ኢትዮጵያ ትራኮማን የማስወገድ ፕሮጀክት አበረታች ስራዎች

   Trachoma Elimination Project  (1)

አመልድ ኢትዮጵያ ከሲቢኤም ኢንተርናሸናል ጋር በመተባበር በደቡብ ወሎ በወረኢሉ፣ጃማ እና ለገሃዲ ወረዳዎች የትራኮማ በሽታን ለማጥፋት ንፁሕ ውሃ አቅርቦት እና የመጸዳጃ ቤቶች ግንባታ ሥራ በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ የውሃ ምንጮችን በማጎልበት ነባር የውሃ ጉድገዶችን በማጠናከር በሶላር ሃይል በመታገዝ የህብረተሰቡን የንፅህ መጠጥ ውህ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ነው፡፡ በጃማ ወረዳ በፀሐይ ሃይል የሚሰራ፣ የአንድ ማጠራቀሚያ ጋን እና የውሃ ማከፋፈያ ታንከር የተገነባለት የገጠር የንጹህ መጠጥ ውሃ መስመር (Rural Pipe System-RPS) በመዘርጋት 8 የውሃ ቦኖዎች ተገንብተዋል፡፡ እንዲሁም በለገሂዳ ወረዳ ከነባር የንጹህ ውሃ ምንጭ 4 የውሃ ማከፋፈያ ቦኖዎች ተገንብተው ለአገልግሎት ውለዋል፡፡

   Trachoma Elimination Project  (2)

በትምህርት ቤቶች የተማሪዎችን ንጽህና ለመጠበቅ እና የትራኮማ በሽታን ለማስወገድ በሦስት /ቤቶች ጾታን መሰረት ያደረጉ ባለሁለት ብሎክ ሽታ አልባ መጸዳጃ ቤቶች ተሰርተው በመጠናቀቅ ላይ ናቸው፡፡

   Trachoma Elimination Project  (3)

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today44
Week220
All139273

Currently are 15 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?