በአመልድ ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የስነ-ንጽህና፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ እና ምግብ ችግር የመቅረፍ ፕሮጀክት 12.42 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፤
በአገር ውስጥ ባለው ግጭት ምክንያት ከኦሮሚያ ክልል፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል እና ከሌሎች አካባቢዎች ተፈናቅለው በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን እና ደቡብ ወሎ ዞን የሚገኙ የጃሬ፣ መካነ-ኢየሱስ እና መርሳ መጠለያ ጣቢያዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተፈናቃይ ይገኛል፡፡ የእነዚህ ተፈናቃዮች ህይወት ለመጠበቅ እና በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የተጎዱ የማህበረሰብ ክፍሎችን ኑሮ ለማሻሻል በአመልድ ኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የስነ-ንጽህና፣ ንጹህ መጠጥ ውሃ እና ምግብ ችግር የመቅረፍ ፕሮጀክት ከጀርመን ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት በቬልት ሁንገር ህልፈ በኩል ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ እ.ኤ.አ በ2023 12,421,200 ብር በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ 1,023 ቤተሰቦች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በተጨማሪም፤
• 150 ኩንታል የስንዴ ዱቄት፣ 15 ኩንታል ክክ እና 500 ሊትር የምግብ ዘይት ለ1000 በመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች (ጃሬ፣ መካነ-ኢየሱስ እና መርሳ) ድጋፍ ተደርጓል፤
• ለ150 ቤተሰቦች የተለያዩ አልባሳት (ብርድ ልብስ እና የስፖንጅ ፍራሽ) ተሰራጭቷል፡፡
• ለ300 ቤተሰቦች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች (የቤት ውስጥ ቁሳቁሶች) ድጋፍ ተደርጓል፡፡
• ለ540 ቤተሰቦች 54 ኩንታል የተሻሻለ የጤፍ ዘር እና 15.79 ኩንታል የእንስሳት መኖ ዘር ተሰራጭቷል፡፡
• ለ104 በጦርነት ምክንያት ጥሪታቸውን ላጡ አርሶ አደሮች 312 የእርባታ ፍየሎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡
• እንዲሁም አንድ የምንጭ ማጎልበት ስራ በመሰራቱ በተሁለደሬ ወረዳ የሚገኙ 543 ተጠቃሚዎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡