መሬት ለህይዎት አማራ ፕሮጀክት
በቢኤምዜድ ድጋፍ፣ በጂአይዜድ እና አመልድ ኢትዮጵያ የሚተገበረው ኃላፊነት የሚሰማው የመሬት ፖሊሲ (GPRLP) ስር የሚተገበረው ኃላፊነት ያለው የመሬት ኢንቨስትመንት አስተዳደር ፕሮጀክት ከአውሮፓ ህብረት ጋር በጋራ ፋይናንስ ይደረጋል፡፡ ልዩ ዓላማው “በገጠር አካባቢዎች ድህነትንና ረሃብን ለመቅረፍ በኢኮኖሚ ኋላ የቀሩ የአማራ ክልል አካባቢዎችን መሬት የማግኘትና የኢንቨስትመንት ተጠቃሚነት በዋናነት ማሻሻል” የሚል ነው።
የሚከተለው ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ዋና ዋና ባለድርሻ አካላትን (የመንግስት ሰራተኞችን ፣ የተመረጡ ባለሀብቶችን እንዲሁም የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት እና የማህበረሰብ ተወካዮችን) አቅም ማጠናከር እና የመሬት የኢንቨስትመንት የቁጥጥር ማዕቀፍን ማሻሻል ነው። እንዲሁም ፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት በተተገበረባቸው የአማራ ክልል ሁለት ወረዳዎች (ደ/ኤልያስ እና ወምበርማ ወረዳዎች)፡-
• 28 ከደን ይዞታዎች ጋር የተያያዙ ግጭቶችን በውይይት እንዲፈቱ አድርጓል፡፡
• 56 የግል እና የወል መሬቶች የድንበር ይገባኛል ግጭቶችን በማህበረሰብ ውይይት መፍታት ተችሏል፡፡
• 8 የባሕር ዛፍ ጥላ በማሳ ላይ በሚፈጥረው ጉዳት ምክንያት የተፈጠሩ ግጭቶች ተወግደዋል፡፡
• 47 ከመሬት ውርስ እና ስጦታ ጋር የተያያዙ የፍርድ ቤት ክርክሮች እና አለመግባባቶች በማህበረሰብ ውይይት ተፈተዋል፡፡