የችግኝ ተከላ እየተካሄደ ነው
አመልድ ኢትዮጵያ በ2015 ዓ.ም ክረምት በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የአካባቢ ደህንነትን እና የደን ሽፋንን ለመጨመር የሚያግዙ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚሰጡ 6.8 ሚሊዮን ችግኞችን ተከላ እያካሄደ ነው፡፡ ከእነዚህ ፕሮጀክቶች መካከል በአመልድ ኢትዮጵያ የቤተክርስቲያን ደንን መሰረት ያደረገ የመልክዓ ምድር መልሶ ማልማት ፕሮጀክት ተከላ አንዱ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ እና ደራ ወረዳ በወል መሬቶች፣ በቤተክርስቲያን ይዞታዎች እና የግል ባለይዞታዎች ላይ የሚተከሉ የአገር በቀል፣ የውጭ ዝርያ እና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሰጪ አትክልት ዝርያ ያላቸው 1.24 ሚሊዮን ችግኞች ተካላ እየተከናወነ ይገኛል፡፡