Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የመዝጊያ አውደ-ጥናት ተካሄደ፤

በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት የመዝጊያ አውደ-ጥናት ተካሄደ፤

       photo 2023-06-27 05-44-14

በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በአማራ ክልል 7 ወረዳዎች (ወልድያ ክላስተር 3 ወረዳዎች - ራያ ቆቦ፣ ሃብሩ እና ጉባ ላፍቶ) መቄት ክላስተር 2 ወረዳዎች (መቄት እና ዋድላ) እና መሃል ሜዳ ክላስተር 2 ወረዳዎች (መንዝ ማማ ምድር እና መንዝ ጌራ ምድር) 36,000 ቤተሰቦችን በምግብ ዋስትና እራሳቸውን እንዲችሉ በማድረግ ከተረጅነት እንዲወጡ ሲሰራ ቆይቷል። ፕሮጀክቱ ከአሜሪካ መንግስት እና ህዝብ በኬር ኢትዮጵያ በኩል በተገኘ $9.92 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ .. ከታህሳስ 2016 - ሰኔ 2023 ሲተገበር ቆይቷል፡፡ የፕሮጀክቱ የመዝጊያ አውደ-ጥናት ሰኔ 19/ 2015 . በደሴ ከተማ ተካሂዷል፡፡

       photo 2023-06-27 05-44-18

በፕሮጀክቱ የመዝጊ አውደ-ጥናት ላይ የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ሲኔር አማካሪ አቶ ደጀኔ ምንሊኩ እንዳሉት የፕሮጀክቱ ስራዎች በጦርነቱ ምክንያት ክፉኛ ቢጎዱም አርሶ አደሮች በስልጠና ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ወደ ነበሩበት መመለስ ይችላሉ ብለዋል፡፡ የአማራ ክልል ገንዘብ ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ደመቀ ቦሩ (.ኤች..) በበኩላቸው አመልድ ኢትዮጵያ በክልሉ በጥራት እና በመጠን የሚሰራቸው ውጤታማ ስራዎችን ለማስቀጠል ሁሉም ፕሮጀክቱ የተተገበረባቸው ወረዳዎች የመንግስት አካላት ቁርጠኛ ልትሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡ በመዝጊያ ፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የኬር ኢትዮጵያ ምክትል ዋና ዳይሬክተር / ሳራ ኸርልበርት እንደገለጹት አመልድ ኢትዮጵያ የኬር ኢትዮጵያ የረዥም ጊዜ አጋር በመሆን በውጤታማነት ፕሮጀክቶችን ስንተገብር ቆይተናል፡፡ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ መሻሻያ ፕሮጀክትም የተጠቃሚዎችን ኑሮ እንዲሻሻል በማድረጉ ልተኮሩ ይገባል ብለዋል፡፡

       photo 2023-06-27 05-44-17

የፕሮጀክቱ ያለፉት 6 ዓመታት አፈጻጸም ሪፖርት በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ክልላዊ አስተባባሪ አቶ ዳኘ ታደሰ ለተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡ በፕሮጀክቱ አማካኝነት 36,186 (ሴት፡ 11,119) ቤተሰቦች በመንደር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቁጠባ በመደራጀት $1.22 ሚሊዮን ቆጥበዋል። እንዲሁም 27,544 (ሴት፡ 10,530) ቤተሰቦች በተመረጡ እሴት ሰንሰለቶች ተሳትፈዋል፤ 33,452 ቤተሰቦች (ሴት፡ 15,153) በተጓዳኝ ስራዎች በመሰማራት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ አግኝተዋል።

       photo 2023-06-27 05-44-22

የፕሮጀክቱ ያለፉት 6 ዓመታት አፈጻጸም ሪፖርት በአመልድ ኢትዮጵያ ለአደጋ የማይበገር የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ክልላዊ አስተባባሪ አቶ ዳኘ ታደሰ ለተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡ በፕሮጀክቱ አማካኝነት 36,186 (ሴት፡ 11,119) ቤተሰቦች በመንደር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቁጠባ በመደራጀት $1.22 ሚሊዮን ቆጥበዋል። እንዲሁም 27,544 (ሴት፡ 10,530) ቤተሰቦች በተመረጡ እሴት ሰንሰለቶች ተሳትፈዋል፤ 33,452 ቤተሰቦች (ሴት፡ 15,153) በተጓዳኝ ስራዎች በመሰማራት ተጨማሪ የገቢ ምንጭ አግኝተዋል።

በፕሮጀክቱ የመዝጊያ አውደ-ጥናት ላይ ከአብክመ ገንዘብ ቢሮ፣ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው ዞኖች፣ ወረዳዎች የሚመለከታቸው ተጠቃሚዎች እና የመንግስት አካላት የአመልድ ኢትዮጵያ ሃላፊዎች እና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today44
Week220
All139273

Currently are 102 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?