አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅቶች ስለአመልድ ኢትዮጵያ ከጻፉት!
ውድ ፈገግታው እና ግርማ
"ስሜ ኤሚሊ ጃኖች እባላለሁ፡፡ እኔ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የኬር አሜሪካ (CARE USA) የአመራር እና የእውቀት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ነኝ። ላለፉት ጥቂት ሳምንታት በአማራ ክልል ከኬር እና የአመልድ ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር የኑሮ ማሻሻያ እና ለአደጋ የማይበገር ፕሮጀክትን በመንድር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቁጠባ (ቬሳ) አባል የሆኑ እና የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ከሆኑ ሰዎች ጋር በመገናኘት የስኬት ታሪኮችን ስንሰራ ነበር፡፡ ተጠቃሚዎች ቀውሱን እንዲቋቋሙ ፕሮጀክቱ እንዴት እንደረዳቸው እና የፕሮጀክቱን ቀጣይነት ለማየት ተጠቃሚ አባውራዎችን እየጠየቅን ነበር።
በጎብጎብ ቀበሌ የሚገኘውን መሰረት ቬሳ ለመጎብኘት ሄድን፤ ሁለታችሁም ተጠቃሚዎች ትምህርት እንዲያገኙ እንዲያገኙ እና ለስኬታቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆናችሁ ነግረውኛል። የእናንተን ስም እየጠሩ፣ በጣም እንደደገፋችኋቸው እና እንዴት ያለማቋረጥ ከእነሱ ጋር ለመስራት እንደምትመጡ፣ ሁለታችሁም ምን ያህል በቅንነት ለውጥ እንዲመጣ መስራታችሁን ነግረውኛል፡፡ ድንች በማምረት ለአካባቢው ህብረት ስራ ማህበራት የሚሸጡት አቶ አድማሱ አለሙ በተለይ እናንተ ምን ያህል ትልቅ ስራ እንደሰራችሁ እና ከእናንተ ጋር መስራት ለእሱ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ተናግሯል። ከእርሱ ጋር ካደረግነው ቃለ ምልልስ ያገኘሁትን እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡-
'እዚህ የሚሰራ የነበረው የአመልድ ኢትዮጵያ የኤክስቴንሽን ፕሮሞተር አቶ ፈገግታው ሚርሃቡ ላመጣነው ስኬት ትልቁን ድርሻ ይወስዳል፡፡ እርሱ በቀን 24 ሰዓት ሳምንቱን ሙሉ ይሰራል፡፡ ደክሞኛል ብሎ አያውቅም፡፡ ስራው አድካሚ ነው ብሎ አያውቅም። በሥራው ሁልጊዜ ደስተኛ ነበር፡፡ አሁንም ፈገግታውን እናስታውሳለን። ፈገግታው በጣም ልዩ ነበር እና ከእሱ ጋር መስራታችን አስደስቶናል። የእኛን ብቻ ሳይሆን ጠንክሮ በመስራት የራሱን ህይወትም አሻሽሏል፡፡ እሱ ለእኛ በጣም ደግ ሰው ነበር፣ እና ሁሉንም ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ ነበር። ሁሉንም ሰው። ድሃ ሆንክ፣ አጭር ሆንክ፣ ረጅም ወይም ወፍራም ወይም ቀጭን ሆንክ ለእሱ ምንም አልነበረም (ማዳላት አያውቅም)። እሱ ለእኛ በጣም አስፈላጊ እና በሙሉ ልባችን የተቀበልነው ሰው ነበር፡፡' ብሎኛል፡፡
የጎበኘናቸው ተጠቃሚዎች አሁንም በጥሩ ሁኔታ እየሰሩ ነበር፣ የተወሰኑ በግጭቱ ተጽዕኖ ሲያጋጥማቸው ወደ ኋላ የተመለሱ ነበሩ፣አሁን እንደገና እራሳቸውን ለመቻል ተቋቁመው እየሰሩ ነው፡፡ አድማሱ በተለይ በጥሩ ሁኔታ እየሰራ ነበር፡፡ የድንች ማሳውን እያለማ ነበር፡፡ አንድ ፕሮጀክት ከተዘጋ ከ6 ዓመታት በኋላም ቢሆን እናንተ ምን ያህል በፍቅር እንደምትታወሱ መስማት እና ጎበዝ ሰራተኞች መኖራቸው ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ሲገልጹ መስማት አስደሳች ነበር። እነዚህን ማህበረሰቦች ለመደገፍ ላደረጋችሁት ነገር እና አሁንም ለምትሰሩት ስራ እናመሰግናለን። በተጨማሪም አቶ ሀብቱ በጉብኝቴ ላይ ድንቅ አድርገህ ስላስተናገድህን በጣም አመሰግናለሁ። (በቆይታዮ) ብዙ ተምሬአለሁ፣ እና በጣም በብዙ ነገሮች ተደንቄያለሁ።"
ከሰላምታ ጋር
ኢሚሊ ጃኖች I CARE USA | Senior Director Thought Leadership and Knowledge Management
1100 17th Street NW Suite 900, Washington, DC 20036
work phone: 202-609-6350 | cell phone: 404-944-2312 | email: This e-mail address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it
care.org | twitter | facebook | get involved