የሮቢት ሁሉን አካታች 1ኛ ደረጃ የአዳሪ ትምህር ቤት በሲቢኤም ጣሊያን የገንዘብ ድጋፍ የተሠራ ነው
አመልድ ኢትዮጵያ ለሮቢት ሁሉን አካታች 1ኛ ደረጃ የአዳሪ ትምህር ቤት ድጋፍ ለሚሹ 55 ተማሪዎች የአልባሳት የምግብ፣የመኝታ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማሟላት ድጋፍ እያደረገ ይገኛል፡፡
የአዳሪ ትምሕርት ቤቱ አንድ የመማርያ ክፍል ሕንፃ፣ አራት ክፍሎች ያሉት ሲሆን አንድ ሕንፃ ደግሞ አምስት የወንዶች እና አምስት የሴቶች የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ክፍሎችን የያዘ ነው፡፡ በተጨማሪም አስር ከፍሎችን የያዘ አንድ ሕንፃ የመፀዳጃ ቤት ከነ ሻወር አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ አንድ ሕንፃ ደግሞ የምግብ አዳራሽ አገልግሎት የሚሰጥ ነው፡፡ በተጨማሪም ለምግብ ማብሰያ ሁለት ክፍሎች ያሉት ሕንፃ (አንዱ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ፤ ሌለኛው በማገዶ እንጨት መጠቀም የሚያሰችል) ተሰርተዋል፡፡ ለተማሪዎች የልብስ ማጠቢያ አገልግሎት የሚሰጡ ገንዳዎች፣ ለውኃ ማጠራቀሚያ የሚያገለግል ሮቶ ከነማስቀመጫው ተዘጋጅቷል፡፡ የውኃ እና የመብራት መስመር በሁሉም ክፍሎች አስፈላጊ በሆነ ስፍራ ዝርጋታ ስራ ተከናውኗል፡፡ አመልድ ኢትዮጵያ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሲሠራ በርካታ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አመልድ ኢትዮጵያን አምነው አብረው የሚሠሩ አሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዱ ሲቢኤም ነው፡፡ ሲቢኤም ብዙ ቤተሰብ አለው፡፡ የሮቢት ሁሉን አካታች 1ኛ ደረጃ የአዳሪ ትምህር ቤት ግንባታ ድጋፍ ያደረገው ሲቢኤም ጣሊያን ነው ፡፡
ሲቢኤም የአማራ ሕዝብ እውነተኛ ወዳጅ ድርጅት ነው፡፡በመጠጥ ውኃ፣በሥነ ንፅህና በሥርዓተ ምግብ በርካታ ሥራዎችን በደቡብ ወሎ እና በደቡብ ጎንደር አብሮ ሲሰራ የቆየ ድርጅት ነው፡፡አሁንም አብሮ እየሠራ ይገኛል፡፡ ለሮቢት ሁሉን አካታች 1ኛ ደረጃ የአዳሪ ትምህርት ቤት ግንባታ መሠረታዊ የገንዘብ ድጋፍ ያደረገው ሲቢኤም ጣሊያን ነው፡፡