Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች በአመልድ ኢትዮጵያ መሬት ለህይወት ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት ጥምረት ክልላዊ ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ።

በአመልድ ኢትዮጵያ መሬት ለህይወት ፕሮጀክት የባለድርሻ አካላት ጥምረት ክልላዊ ጉባኤ በባህር ዳር ከተማ ተካሄደ።

    Land for Life Project Stakeholder’s Regional Conference (1)

በአመልድ ኢትዮጵያ መሬት ለህይዎት ፕሮጀክት ከረጅም ጊዜ አጋር ከሆነው ቬልት ሁንገር ህልፈ/welthungerhilfe ጋር በመተባበር ከጂአይዚ /GIZ/ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በክልሉ በተመረጡ ሁለት ወረዳዎች ማለትም በደብረ ኤልያስ እና በወንበርማ ወረዳዎች ውስጥ የመሬት ለህይወት-አማራ ፕሮጀክትን በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ የመሬት ፍትሃዊ አጠቃቀምን ለማስፈን እና ችግሮችን ለመፍታት በክልል ደረጃ የባለብዙ ድርሻ አካላትን፣ በወረዳ እና በቀበሌ ደረጃ ደግሞ የማህበረሰቡ፣ የባለሃብቱ እና የመንግስት አካላትን ያቀፈ ፎረም (CIGF- ሲአይጂኤፍ) አቋቁሞ የመሬት አጠቃቀም እና ባለቤትነት ጥያቄዎችን ፍርድ ቤት ሳይሄዱ በፎረሙ በኩል በሽምግልና እንዲፈቱ በማድረግ ትልቅ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡

    Land for Life Project Stakeholder’s Regional Conference (2)

የፕሮጀክቱ ክልላዊ ጉባኤ ባሕር ዳር ከተማ መጋቢት 18/ 2015 . ተካሂዷል፡፡ በጉባዔው የአመልድ ኢትየጵያን የስራ ኃላፊዎች ጨምሮ የክልሉ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎች፣ የሲቭል ማህበረሰብ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ፕሮጀክቱ ከሚተገበርባቸው ዞኖችና ወረዳዎች የመሬት አስተዳደር ኃላፊዎችና ባለሙያዎች፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች፣ ኢንቨስተሮች የረጅ ድርጅቶች ኃላፊዎችና ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ባላድርሻ አካላት ተገኝተዋል፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለማየሁ ዋሴ ጉባዔውን በንግግር ሲከፍቱ እንደሉት የመሬትን ሃብት በአግባቡ ከመጠቀም ውጭ መጠኑን ልንጨምረው የማንችለው ብቸኛ ሃብት መሆኑን ገልጸው ውጤታማ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲኖር ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ ማድረግ እንደሚገባቸው ተናግረዋል፡፡ ከኢንቨስትመንት አኳያም ቢሆን የሚስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በአርሶ አደሩና በኢንቨስተሩ መካከል የሚታዩ ችግሮቸን በመለየት የተሻለ ስራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ከዚህ አኳያ ይህመሬት ለህይወትፕሮጀክትም ከመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም እንዲሁም ከኢንቨስትመንት አኳያ በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ኤሊያስ እና በምዕራብ ጎጃም ዞን ወንበርማ ወረዳዎች እየሠራ ነው ብለዋል። ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው ወረዳዎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችና ሌሎችም የመሬት ባለቤትናትና የመጠቀም መብታቸውን አጥተው የነበሩ ግለሰቦች የመሬት ባለቤትነታቸው እንደተመለሰላቸውና መጠቀም መቻላቸውን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የአማራ ክልል ኢንዱስተሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ መሬት ለሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል። ኃላፊው አክለውም ኢንቨስተሮች ኢንቨስት ሲያደርጉ የማህበረሰቡን ጥቅም በማስቀደም መሆን እንዳለበት ገልጸው እንደዚህ ዓይነት ፕሮጀክቶች በማህበረሰቡና በኢንቨስተሩ መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲኖር ሚናቸው ጉልህ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

    Land for Life Project Stakeholder’s Regional Conference (3)

ፕሮጀክቱን ውጤታማና ቀጣይነት ያለው ለማድረግ ሌሎች ተያያዥ ስራዎችን ለመስራት መሬት ለህይወት የአማራ ባለድርሻ አካላት ጥምረት በሚል 14 አባላት ያሉት ጥምረት ተቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡  

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today2
Week70
All134764

Currently are 18 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?