የአመልድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ አመራሮች በጦርነት ለተጎዱ ነዋሪዎች የተደረገውን ድጋፍ ጎበኙ
አመልድ ኢትዮጵያ በወልዲያ ማስተባበሪያ ቅ/ጽቤት ባሉ ወረዳዎች ስር ያሉ ነዋሪዎች በጦርነት ወቅት ተፈናቅለው ለከፋ ኑሮ መጎሳቆል ተዳርገው ነበር፡፡ በመሆኑም ይህን ችግር ለመቅረፍ አመልድ ኢትዮጵያ በሲአርኤስ በኩል ከአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በጦርነት ለተፈናቀሉ 60 ሺህ ነዋሪዎች የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አድርጓል፡፡ ከጦርነት ማግስት ተፈናቅለው ለችግር ለተጋለጡ ተጠቃሚዎች በአጠቃላይ 459 ሺህ 591 ኩንታል ጥቅል እርዳታ ተደርጓል፡፡ እንዲሁም በጦርነቱ ጥሪታቸውን ላጡ ለአርሶ አደሮች ጥሬ ገንዘብ በመስጠት በበግ እርባታ እንዲሰማሩ ተደርጓል፡፡
የአመልድ ኢትዮጵያ የማኔጅመንት አባላት ከማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰራተኞች ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ተደረገውን ድጋፍ በመስክ ጉብኝት አድርገዋል፡፡