በአመልድ ኢትዮጵያ የደህንነት ጥበቃ ፖሊሲ ላይ ስልጠና ተሰጠ፤
የአመልድ ኢትዮጵያ የደህንነት እና ጥበቃ ፖሊሲ የድርጅቱ ሰራተኞች እና ተጠቃሚዎች ደህንነት እና መብት ከጥቃት ለመጠበቅ ማለትም ከጾታዊ ጥቃት፣ አካላዊ ጥቃት፣ የስነ-ልቦና ጥቃት፣ በህገወጥ የሰዎች ዝውውር የመብት ጥሰት እና በአግባቡ ደንበኛን አለማስተናገድን ያካትታል፡፡ በስልጠናው የደህንነት እና ጥበቃ ፖሊሲው መርሆዎች ለሰራተኞች ተዋውቀዋል፡፡ ጾታዊ ትንኮሳ ማካሄድ፣ ማንኛውም ሰራተኛ ከ18 ዓመት በታች ህጻናት ጋር ጾታዊ ግንኙነት መፈጸም፣ የስራ ኃላፊነትን በመጠቀም ጾታዊ ጥቃት መፈጸም፣ ወዘተ. ማድረግ አይገባም፡፡ እንዲሁም ፕሮጀክቶች በሚተገበሩበት ወቅት በተጠቃሚዎች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ እንዳይኖራቸው ማድረግ ይገባል፡፡ ከደህንነት እና ጥበቃ ጋር በተያያዘ ችግሮች ከተፈጠሩ ደግሞ ለሚመለከተው የስራ ክፍል ማለትም ለዋና ጽ/ቤት የደህንነት እና ጥበቃ ባለሙያ፣ ለዋና ዳይሬክተር፣ ለሰው ሃይል መምሪያ ማናጀር እና ለቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የደህንነት እና ጥበቃ ተጠሪ ባለሙያዎች ሪፖርት ማድረግ ይቻላል፡፡