Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች በአመልድ ኢትዮጵያ የመሬት ለህይወት አማራ ፕሮጀክት ስልጠና ተሰጠ

  በአመልድ ኢትዮጵያ የመሬት ለህይወት አማራ ፕሮጀክት ስልጠና ሰጠ

     Training given on international guidelines 1

በአመልድ ኢትዮጵያ የመሬት ለህይወት አማራ ፕሮጀክት ሃላፊነት የተሞላበት የግብርና ኢንቨስትመንት፣ በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ የመሬት ይዞታ አስተዳደር እና የብሄራዊና ክልላዊ የመሬት ህግጋት አፈጻጸምና በሚስተዋሉ ክፍተቶች ዙሪያ ከግንቦት 19- 28/2014 . ለተከታታይ 8 ቀናት ስልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ በጂአይዜድ የገንዘብ ድጋፍ (8 ሚሊዮን ብር በላይ) ስትራቴጂክ አጋሩ ከሆነው ቬልት ሁንገር ሂልፈ (WHH) ጋር በመተባበር የመሬት ለህይወት አማራ ናሙና ፕሮጀክት በአማራ ክልል በተመረጡ የወምበርማ እና ደብረ ኤልያስ ወረዳዎች ከታህሳስ/2012 . እስከ ጥቅምት/2015 . ድረስ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል።

     Training given on international guidelines 2

የዚህ ፕሮጀክት ዋና ዓላማ በኢትዮጵያ ውስጥ ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ዓለም አቀፍ አሰራሮችና ልምዶችን ተግባራዊ በማድረግ ኃላፊነት የተሞላበት የግብርና ኢንቨስትመንትና የመሬት ይዞታ አስተዳደር ሥርዓትን በመዘርጋት ብሎም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፅኦ ማበርከት ነው፡፡

በተለይ ከመሬትና መሬት ነክ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የሚስተዋሉ የህግጋት አፈጻጸም ክፍተቶችን በውል በመለየት ህዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርግ የፖሊሲ ማሻሻያ ሃሳቦችን ማመንጨትና ለመንግስት ግብዓትነት የሚውሉ ምክረ-ሃሳቦችን በማቅረብ አነስተኛ ማሳ ያላቸው አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ሌሎች ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለይ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አረጋዊያን፣ የአካል ጉዳተኞች፣ ወጣቶች እና በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማሩ ባለሃብቶች ተጠቃሚ እንዲሆኑና ኑሯቸው እንዲሻሻል የድርሻውን ይወጣል፡፡

የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ማን ነው?

በደብረ ኤልያስ እና ወንበርማ ወረዳዎች 230 ሺህ ህዝብ/አርሶአደር ከመሬት ይዞታ አስተዳደር ጋር የተጎዱ (ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጎጅዎች) በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

     Training given on international guidelines 4

የሚመለከታቸው አካላትም (በክልልና በወረዳ ደረጃ ያሉ የመንግስት አጋር አካላት፣ የሲቪክ ማህበራት፣ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ ባለሀብቶች በመሬት ለህይወት የአማራ ክልል ማፕ ባመቻቸላቸው የባለብዙ ተዋናዮች ተሳትፎ ምክንያት በፖሊሲዎች፣ ህጎች እና የአሰራር ለውጦች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

እንደ ከተማ መስፋፋት ምክንያት የልማት እንቅስቃሴዎች የተፈናቀሉና ተጎጂ የሆኑ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የገጠር ከተማ ነዋሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ።

     Training given on international guidelines 3

በፕሮጀክቱ ፈጻሚዎችና ለጋሸ ድርጅት ጋር በፕሮጀክቱ ራእይ፣ ዓላማዎች፣ አፈጻጸም እና የእርስ በርስ ሚናዎች ላይ ግልጽነት የተፈጠረ ሲሆን መደበኛ የሆነ መስተጋብርና ቅንጅት ወሳኝ እንደሆነም ተጠቁሟል። በፕሮጀክት አሰራር ዙሪያ የተለያዩ ጥያቄዎችና ሃሳቦች ተነስተው በጥልቀት ውይይት ተደርጎባቸው የፕሮጀክቱን የመጨረሻ ግብ ለማሳካትም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።

በአመልድ ኢትዮጵያ፣ ቬልት ሁንገር ሂልፈ (WHH) እና ጂአይዜድ አማካኝነት በተዘጋጀው ስልጠና ተጎጂ የሆኑ ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች፣ የአነስተኛ መሬት ባለይዞታዎች፣ ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወረዳ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today58
Week234
All100763

Currently are 7 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?