Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች በአረንጓዴ ቤት ቴክኖሎጅ አትክልት እና ፍራፍሬ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ፤

በአረንጓዴ ቤት ቴክኖሎጅ አትክልት እና ፍራፍሬ በማልማት ተጠቃሚ መሆናቸውን አርሶ አደሮች ተናገሩ፤

       greenhouse technology

በኢትዮጵያ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ ከፍተኛ የሆነ የእርሻ መሬት ጥበት እና መበጣጠስ እያጋጠመ ይገኛል፡፡ ተጨማሪ የእርሻ ማሳ ለማግኘት በያመቱ ደን ይጨፈጨፋል፡፡ መፍትሄውም በትንሽ ማሳ ላይ ዘመናዊ ግብርና ማካሄድ ነው፡፡ በአመልድ ኢትዮጵያ የተጎዱ የደን መሬቶችን መመለስ እና ማልማት ፕሮጀክት ከኖሮዌ የደን ልማት ማህበር ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በአማራ ክልል 4 ወረዳዎች (እብናት፣ ሊቦከምከም፣ ፋርጣ እና ቋሪት ወረዳዎች) የሚገኙ አርሶ አደሮችን በአረንጓዴ ቤቶች የአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲያለሙ እያደረገ ይገኛል፡፡ በአረንጓዴ ቤቶች አትክልትን ማልማት ከተባይ ለመከላከል፣ አስፈላጊውን ሙቀት ለመመጠን እና ከመጥፎ አየር ንብረት በመከላከል ጥራትና ብዛት ያለው ምርት ለማምረት ምቹ ናቸው፡፡ በዚህም አርሶ አደሮች በትንሽ ማሳ አመቱን በሙሉ ሐቫቭ እና ቲማቲም በማምረት ለተጠቃሚዎች እያደረሱ ነው፡፡

       greenhouse technology1

ከተጠቃሚዎች መካከል በሊቦከምከም ወረዳ የሚገኙት ወጣት አርሶ አደር ወርቁ ጀምበር እና ቄስ አርሶ አደር አማረ ሙሉ ከፕሮጀክቱ ባገኙት ስልጠና እና የቁሳቁስ ድጋፍ በአረንጓዴ ቤት ቴክኖሎጂ የጓሮ አትክልቶችን እያለሙ ነው፡፡ ወጣት ወርቁ እንዳለው ባለፈው በጋ 126 . የአረንጓዴ ቤት ሐቫቭ በማልማት ለገበያ አቅርቦ 6ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል፡፡ 2 ዙር ክረምት ቲማቲም እያለማ ሲሆን ምርቱን ለገበያ ማቅረብ ጀምሯል፡፡ በተመሳሳይ ቄስ አማረ የአረንጓዴ ቤት ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቲማቲም እያለሙ ነው፡፡ የቲማቲም ምርታቸውም በመብሰሉ በተመጣጣኝ ዋጋ ለተጠቃሚዎች እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

በአጠቃላይ በዚህ በጀት ዓመት ፕሮጀክቱ ለአርሶ አደሮች 31 አረንጓዴ ቤቶችን በመገንባት 44.85 ኩንታል ሐቫቭ እና 80.5 ኩንታል ጥቅል ጎመን አምርተው ገቢ እንዲያገኙ ሰርቷል፡፡ በተጨማሪም በፕሮጀክቱ አማካኝነት 983,621 የተለያዩ ቋሚ አትክልቶች እና አገር በቀለ ችግኞች በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ ተተክሏል፤ 863 ሄክታር የተጎዱ ተፋሰሶች ከእንስሳት ንክኪ ነፃ በማድረግ ችግኝ ተተክሎባቸው እያገገሙ ነው፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today61
Week155
All83649

Currently are 26 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?