Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች የቻሪቲ ዋተር ፕሮጀክትና ተስፋ ሰጭ ውጤቶቹ

          የቻሪቲ ዋተር ፕሮጀክትና ተስፋ ሰጭ ውጤቶቹ

       Bassona Worana Woreda 4

በአመልድ የቻሪቲ ዋተር ፕሮጀክት በተሳትፏዊ መማማርና መተግበር ተስፋ ሰጭ ውጤቶች እየታዩ ነው።

አመልድ ኢትዮጵያ ከቻሪቲ ዋተር ጋር በመተባበር በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ባሶና ወራና ወረዳ ላለፉት ሶስት ዓመታት የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ የግል እና የአካባቢ ንፅህና አገልግሎት እንዲያሟላ ሲሰራ ቆይቷል።

.. 2021 ብቻ ፕሮጀክቱ 79 ጥልቅ ጉድጓዶችን 10 ምንጮችን እና 4 መፀዳጃ ቤቶችን በማጠናቀቅ ላይ ሲሆን በተለይ የውሃ እና የንፅህና ችግር ጎልቶ በሚታይባቸው አካባቢዎች 30 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ያደርጋል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት (.. 2019 እና 2020) ፕሮጀክቱ በሲያ ደብርና ዋዩ በባሶና ወራና እና በአንጎለላና ጠራ ወረዳዎች 68.8 ሚሊዮን ብር 172 የውሃ ተቋማትን በማልማት በአጠቃላይ 55 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ አድርጓል።

       Bassona Worana Woreda 1

እንደሌሎቹ የአገሪቱ ገጠራማ አካባቢዎች በቦሶና ወራና ወረዳ ውስጥ ንጽህናው የተጠበቀ ሽታ አልባ የመጸዳጃ ቤት አጠቃቀም ዝቅተኛ ነው፡፡ ማህበረሰቡ በቤተሰብ ደረጃ የተሻሻለ የመፀዳጃ ቤት ባለቤት እንዲሆን ለዓመታት ሲሞክር ቆይቷል። ሆኖም ህዝቡ በዚህ ረገድ ተግባራዊ ለውጦችን ማሳየት አልቻለም።

የጤናውን ዘርፍ ፈታኝ ካደረጉት ችግሮች አንዱ የሆነው በየቦታው የመጸዳዳትና ከአይነ ምድር ጋር በተያያዘ የሚከሰቱ በሽታዎች በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡ ችግሮችን ለመቅረፍ የአመልድ ቻሪቲ ዋትር ፕሮጀክት የንጹህ መጠጥ ውሃ እያጎለበተ ይገኛል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የማህበረሰቡን የግል እና የአካባቢ ንፅህና ለመጠበቅ ልዩ ልዩ ስራዎችን በትኩረት እያከናወነ ነው። ፕሮጀክቱ የአከባቢውን ማህበረሰብ ንፅህና አጠባበቅ ልምዶችን ለማዳበርና የውሃ አስተዳደርና አጠቃቀም ልምዶችን ለማሻሻል ተሳትፏዊ መማማርና መተግበር (PLA) የተባለ አዲስ ስልት ተግባር ላይ አውሏል።

       Bassona Worana Woreda 3

.. ከጥር 2021 ጀምሮ በቦሶና ወራና እና በሲያ ደብርና ዋዩ ወረዳዎች በአጠቃላይ 16 መንደሮችን/ጎጦችን በማካተት ተሳትፏዊ መማማርና መተግበር (PLA) እየተሰራ ሲሆን ማኅበረሰቡ የተሻለ ግንዛቤ እና የአመለካከት ለውጥ እያሳየ ነው፤ በአሁኑ ሰዓት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችም እየታዩ ነው። የግልና አካባቢ ንፅህና አጠባበቅ ተቋማትን/የውሃ ተቋማትን የመጠገን፣ አጥር የማጠር፣ በየወሩ ገንዘብ የማዋጣትና በጥንቃቄ የመጠቀም ልምድ ተሻሽሏል፡፡

ለበሽታ መከሰት ዋነኛ መንስኤ የሆነው በየቦታው መጸዳዳትን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረትና ጤናማ ህብረተሰብ ለመፍጠር የተሻሻለ መጸዳጃ ቤት ወሳኝ ነው። የውሃ ተቋማትና መፀዳጃ ቤቶች በንጽህና እንዲገነቡና እንዲያዙ ተግባራዊ ትምህርትና ስልጠና እንዲወስዱና ዘላቂነት ያለው ውጤት እንዲመጣ እየተደረገ ነው።

       Bassona Worana Woreda 2

አርሶ አደር ተክለዮሐንስ ዳኜ ባለትዳርና የአራት ልጆች (ወንድ 3 ሴት 1) አባት ሲሆኑ በባሶና ወራና ወረዳ ባቄሎ ቀበሌ አመፀኛ ጎጥ ነዋሪ ናቸው። አርሶ አደሩ ሲናገሩ "እኔ ስለግልና አካባቢ ንፅህና እንዲሁም ተዛማጅ በሽታዎች በቂ ግንዛቤ አልነበረኝም። ባገኘነው ቦታ ሁሉ እንጸዳዳ ነበር። የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኛዋ መጸዳጃ ቤት እንድገነባ አስገድዳኝ ነበር፤ ነገር ግን እኔን የሚጠቅም ስላልመሰለኝ አልተቀበልኋትም ነበር። የመጸዳጃ ቤት ባለመስራቴም በገንዘብ ተቀጥቻለሁ፡፡ በቅጣት አላምንም፤ እኔንም ሳይለውጠኝ ቆይቷል።"

ይሁን እንጅ የአመልድ ቻሪቲ ዋትር ፕሮጀክት ከኅዳር 2013 . ጀምሮ በተሳትፏዊ መማማርና መተግበር (PLA) ስልት ከሰለጠኑ በኋላ የውሃ ተቋማት አያያዝ የመፀዳጃ ቤት (በቤተሰብ እና በተቋማት ደረጃ) ወሳኝ መሆኑን ተገነዘቡ። በአሁኑ ሰዓት አቶ ተክለዮሐንስ የኮንክሪት መፀዳጃ ቤት እና መታጠቢያ ቤት ገንብተዋል። በተጨማሪም ጎረቤቶቹ የመፀዳጃ ቤት እንዲገነቡ እና የውሃ ተቋማትን በዘላቂነት እንዲጠቀሙ ምክር እየሰጡ ነው።

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today62
Week156
All83650

Currently are 33 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?