Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች ንጹህ ውሃ- በመናኽሪያ መንደር

                ንጹህ ውሃ- በመናኽሪያ መንደር

           Water access

በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ ጎባጣ-አቅና ቀበሌ 41 አመት የሆነች / እመነሽ ሽፈራው ንፁህ ውሃ ስትቀዳ አገኘናት፡፡ እርሷ እና ጎረቤቶቿከሩቅ ከሚገኝ የጉድጓድ ውሃ እና ንፁህ ካልሆነ ምንጭ እየቀዱ ሲጠቀሙ እንደነበር ነገረችን፡፡ እንደ እርሷ ገለፃ የውሃ ወረፋ ስታስብ መጥፎ ስሜት ተሰማት፡፡ አንዳንድ ጊዜ በመጀመሪያ ወረፋ በሚይዙ ሰዎች ምክንያት እስከ 60 ወይም 70 እንስራ እስኪቀዱ ድረስ እንድትጠብቅ ተገዳለች ፡፡

/ እመነሽ አሁን ታላቅ ደስታ ይሰማታል፡፡ ምክንያቱም ከመኖሪያ ቤቷ አጠገብ በቂ የሆነ ንፁህ ውሃ አግኝታለች፡፡ የውሃ ተቋሙ የተገነባው በአመልድ ጆን ሪግ ዋሽ ፕሮጀክት ከቬልት ሁንገር ሂልፈ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በቪቫ ኮን አግዋ በኩል ነው፡፡

ልጆቿ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ላይ ለረጅም ወረፋ ወደ ሜዳ ሲሄዱ አስታወሰች፡፡ "ከረጅም ርቀት ያልተጣራ የምንጭ ውሃ እንቀዳ ነበር፡፡ የምንጠጣው ውሃ እንኳን ንፁህ አልነበረም፡፡ ልጆቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው ውሃ ለመቅዳት ወደ መስክ መውጣት ግዴታ አለባቸው፡፡ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለፍነው፡፡ ቀደም ሲል የውሃ አጠቃቀምን በተመለከተ ስሜታዊ ነበርኩ፡፡ ቤት ውስጥ ልጆች ውሃ ሲጠልቁ አስጠነቅቃቸዋለሁ፡፡ ፕሮጀክቱ እንደጀመረ ውሃ ለመገንባት መሆኑን ስንሰማ ከመጓጓታችን የተነሳ አላመንንም ነበር፡፡ አሁን ግን በሰፈሬ ባለአራት ፎሴት የውሃ ማከፋፈያ ቧንቧ ውሃ ስላገኘን ነገሮች ተለውጠዋል፡፡ ቤቴ ውስጥ ብዙ ንጹህ ውሃ አለብላለች፡፡

            Water access1

የጎባጣ-አቅና ጥልቅ የጉድጓድ ውሃ በሰከንድ 20 ሊትር ያመነጫል፡፡ የመንሃሪያ መንደር ነዋሪዎች የሚፈልጉት በሰከንድ 4.94 ሊትር ነው፡፡ በዚህም የመንደሯ ኗሪዎች ቁጥር ቢጨምር የሚፈጠር የውሃ እጥረት የለም፡፡ ለማህበረሰቡ የተገነባው የጥልቅ ጉድጓዱ 10 የውሃ አከፋፋይ ማዕከሎች እያንዳንዳቸው 32 የውሃ ፎሴቶች ያሉት ነው፡፡ በተጨማሪም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና ክሊኒኮችን ተጠቃሚ ለማድረግ 4 ነጠላ የውሃ ፎሴቶች ያሉት ማከፋፈያ ተገንብቷል፡፡ ጥልቅ የውሃ ጉድጓዱ 3 ሺህ የሚጠጉ ተጠቃሚዎችን ያገለግላል፡፡

ፕሮጀክቱ 2009 እስከ 2012 . 72 የውሃ ተቋማትን (5 ጥልቅ ጉድጓዶች 46 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ ጉድጓድ) ገንብቶ 64,585 በላይ ተጠቃሚዎችን ከንፁህ ውሃ ችግር አውጥቷል፡፡ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን ንፅህና ለመጠበቅ 10,481 ትምህርት ቤት ማህበረሰብ አባላት የሚያገለግል 22 ብሎክ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤት ገንብቷል፡፡ በተጨማሪም ለቀበሌ ማዕከላት 56 የሞዴል አየር ማስገቢያ የጉድጓድ መፀዳጃ ቤት ገንብቷል፡፡

ፕሮጀክቱ በምስራቅ ጎጃም ዞን 5 ወረዳዎች የውሃ ተቋም ግንባታ የንፅህና እና ንፅህና ተግባራት ላይ ሲሰራ ቆይቷል ፡፡ በአጠቃላይ 8.8 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት መድቦ በጎዛምን ማቻከል ደብረ-ኤልያስ አነደድ እና ስናን ወረዳዎች ላይ 2009 እስከ 2016 . ድረስ 205 ህዝብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እየሰራ ነው፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today1
Week67
All71570

Currently are 15 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?