ፀደይ ባንክ በአማራ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ: ኅዳር 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ፀደይ ባንክ በአማራ ክልል በዋግኽምራ እና በሰሜን ጎንደር ዞኖች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጎል። የባንኩ ዋና ፕሬዚዳንት መኮንን የለውምወሰን ድጋፉ በአመልድ ኢትዮጵያ በኩል ለተጎጂዎች አንዲደርስ አስረክበዋል።
የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ዓለማየሁ ዋሴ (ዶ.ር) ከ450 ሺህ በላይ አስቸኳይ የዕለት ምግብ የሚፈልጉ ወገኖች ስለመኖራቸው ጠቁመዋል። በፀደይ ባንክ በኩል የቀረበው ድጋፉም አስፈላጊ በመሆኑ ባንኩን አመስግነዋል።
ዶክተር ዓለማየሁ ሌሎች ባንኮች፣ ድርጅቶች፣ ተቋማት እና ባለሃብቶችም ድጋፍ በማድረግ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን መታደግ እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል።
ምንጭ:- አሚኮ
Read more: “No More Circumcision Hereafter,” W/ro Eniyat Chane
A project has been carried out in enhancing youths wage employability capacity and self-employment opportunities in Jamma woreda of South Wollo zone