"ከሰለጠንሁ በኋላ የባህርይ ለውጥ አምጥቻለሁ"፣ አርሶ አደር ጀጃው አሰፋ
በማህበረሰቡ ዉስጥ የተዛቡ የስርዓተ ፆታ አመለካከቶች እና ልማዳዊ ድርጊቶች የሴቶችን ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውን አቀጭጮታል፡፡ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ደግሞ የማህበረሰቡ የአስተሳሰብ ለውጥ በተለይም የወንዶች የባህርይ ለውጥ ወሳኝ ነው፡፡
በመሆኑም የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ፤ የአመራርነት እና ዉሳኔ ሰጭነት ለማሻሻል እንዲቻል አመልድ ኢትዮጵያ ከዓለም ብርሃን ራስ አገዝ የማህበረሰብ ልማት ማህበር ጋር ጥምረት በመፍጠር እና በመተባበር ከሲቪል ሶሳይቲ ሳፖርት ፕሮግራም የገንዝብ ድጋፍ በአማራ ክልል በተመረጡ 2 ወረዳዎች (ማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምዕራብ በለሳ እና ምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሣር ምድር ወረዳ) የሴቶችን ፖለቲካዊ ተሳትፎ በማብቃት የአመራር እና ዉሳኔ ሰጭነት አቅም ለማሻሻል ፕሮጀክት በመተግበር ላይ ነው፡፡
ፕሮጀክቱ ከማህበረሰቡ መካከል ለአመቻቹች ስልጠና መበስጠት በወር 2 ጊዜ ሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለማሳድግ ውይይት ይደረጋል፡፡ ከአመቻቾች መካከል በምዕ/በለሳ ወረዳ አምስተያ ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ጀጃው አሰፋ ይገኙበታል፡፡ ከፕሮጀክቱ ባገኙት ስልጠና መሰረት ለአባውራዎች በወር 2 ጊዜ ወር በ8 ቀን እና በ27 ቀን የሴቶችን ውሳኔ ሰጭነት እና የእኩልነትን ለማስፈን ውይይት እናካሂዳለን ብለዋል፡፡
አርሶ አደር ጀጃው በአንድ ወቅት በውይይታቸው ስላጋጠማቸው ነገር እንዲህ ብለዋል፤ "ከቀበሌያችን ባልና ሚስቶች ተፋቱ፤ ባሏ የሚስቱን መሬት፣ ከብት እና አጠቃላይ ንብረቷን በመቀማት ከቤት አስወጣት፡፡ በጣም የከፋ የነበረው ነጠላዋን ሁሉ በእሳት አቃጥሎታል፤ እኛ ነገሩን ስንሰማ ባለቤቷን አገኘነው፡፡ በሰለጠነው መሰረት ባለቤቷን በውይይት አሳምነን መሬቷን እና ከብቶቿን እኩል እንዲያካፍላት አድርገናል፡፡ ሴቷ አሁን መንኩሳ በህይዎት አለች፤ ዘወትር ታመሰግነናለች" ብሏል፡፡
"በፕሮጀክቱ ከሰለጠንሁ በኋላ የባህርይ ለውጥ አምጥቻለሁ፡፡ ከዚህ በፊት ባለቤቴ አግዘኝ ስትለኝ አላውቅልሽም ነበር የምላት፡፡ አሁን ግን ሚስቴ 2 ጊዜ ስትወልድ እኔ ነኝ ያረስኋት (የተንከባከብኋት)፡፡ ገንፎ አገንፍቼ፣ የደም ጨርቋን (በወሊድ ወቀት የተጠቀመችበትን) ሆጣ ወንዝ አጥቤ ነው የተንከባከብኋት፡፡"
አርሶ አደር ጀጃው እንዳለው አሁን የእርሱ ቤተሰብ መተሳሰብ፣ መተዛዘን እና ፍቅር ጨምሯል፡፡