Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ መምሪያ የዕቅድ፣ ክትትል፣ ግምገማና መማማር ፕሮግራም

የልማት ሃብት ማስፋፊያና ምርምር ፕሮግራም 

አመልድ ለትርፍ ያልተቋቋመ፤መንግስታዊ ያልሆነ ሰብዓዊ የልማት ድርጅት በመሆኑ የራሱ የሆነ ገቢ ወይም ከመንግስት የሚመደብለት በጀት የለውም፡፡ በመሆኑም የቆመለትን ዓላማ ለማሳካት የሀብት ምንጩ  ለተመሳሳይ ዓለማ በየወቅቱ ከሚዘረጋው ዓለምዓቀፋዊና ሀገራዊ የዕርዳታና የልማት ሀብት ምንጭ ነዉ፡፡ ይሁን እንጅ ይህ ሀብት በዓለም ደረጃ ካለው ችግርና ሀብቱን ለመጋራት ከሚፈልጉት ባለድርሻዎች አንጻር ሲታይ እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ ከፍተኛ ፉክክርና ውድድር የሚታይበት መሰክ ሆኗል፡፡ ይህን ፉክክር የበዛበትን ውድድር አሸናፊ ሆኖ ካለው ሐብት ለመጋራት፡-

 • የሃብትምንጮችን መለየት
 • የለጋሾችን መመዘኛና አሰራር መረዳት
 • የለጋሾችን ቀልብ የሚስብ የፕሮጀክት ሀሳብና ዕቅድ ማቅረብ ይጠይቃል፡፡

ይህን መሰል ሂደት አልፎ የሚገኝ ሀብት ሲኖር ድጋፉን ዘላቂና አስተማማኝ ለማድረግ አመልድ ብቃት ያለው የፕሮጀክት አፈጻጸም ማሳየት ይጠበቅበታል፡፡ ብቃት ያለው የፕሮጀክት አፈፃፀም ከሚለካባቸው አብይ መለኪያዎች፡-

 • ወቅቱን የጠበቀና ጥራት ያለዉ የአፈጻጸም ሪፖርት
 • የሀብትና የሥራ/ውጤት ጥምርታ ሚዛናዊነት
 • ለማህበረሰቡና ለአካባባው የሚሰጠው ጥቅም አዋጭና ዘላቂነት
 • በሰዎች ላይ የተፈጠረ የኑሮና የህይወት ለውጥ ለወደፊት የሚሰጠው ልምድና ተሞክሮ ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በእነዚህ ሂደቶች መማማርን መሰረት ያደረገ የመረጃ ልውውጥና የመረጃ ፍሰት እንዲኖር ያሻል፤ ከተግባራዊ ምርምርና ተሞክሮ ቀጣይ የልማት ርምጃዎችን ማሻሻልና ማስፋት ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን በተለያዬ ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት በብቃትና በጥራት ለማከናወን በ4 የስራ ክፍሎች የተደራጀ ፕሮግራም በመፍጠር አመልድ ታሪካዊ ኃለፊነቱን ለመወጣት ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኝ ሲሆን እነዚህ የሥራ ክፍሎች፡

 • ሀብት ማሰባሰብ/የፕሮጀክት ዝግጅት
 • ሀብት አሰተዳደር
 • መረጃ አያያዝና አጠቃቀም
 • ክትትል፣ ግምገማና መማማር ናቸው፡፡

ይህ ጥረቱ ከዓመት ዓመት እድገት በማሳየት ላይ ሲሆን በተለይም ከ2001/2002 – 2005/2006 (እ.ኢ.አ) ባለው የሦስተኛው ስተራቴጄክ ዕቅድ ዘመን በሃብት ማሰባሰብ ረገድ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበበት ጊዜ ነው፡፡ እንደዚሁም ከጥር 2001 እስከ ሰኔ 2004 ዓ.ም ባለው ጊዜ፡-

 • ሁለትመቶ (25 የተቀናጀና ከሁለት አመት በላይ ዕድሜ ያላቸው፤ 75 በተወሰኑ መስኮችና የአጭር ጊዜ) ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ 1.2 ቢሊዮን ብርና 18600 ሜ.ቶን እህል ለማንቀሳቀስ ተችሏል፡፡ በዚህ ሂደት ከሁለት ታላላቅ የበይነ-መንግስታት ለጋሾች (ከስዊድን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብርና ከአሜሪካ የልማት ተራዲኦ ደርጅቶች) ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ለመመስረት ተችሏል፡፡
 • ለ120 የአመልድና ለ200 የመንግስት ባለሙያዎች በዕቅድ፣ ክትትል፣ ግምገማና መማማር እንደዚሁም በፕሮጀክት ቀረጻና ሪፖርት አሰራር ላይ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

10 የተቀናጁ የክትትል መስክ ጉብኝቶቾ በፕሮጀክቶችና ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች ላይ ተካሂደዋል፡፡