Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ መምሪያ ኮሙኒኬሽን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት

የኮሙኒኬሽን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎት

የኮሙኒኬሽን ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አገልግሎቱ ዋነኛውና ቀዳሚው ተግባሩ የድርጅቱን ማንነትና መልካም አፈፃፀሙን የተመለከቱ መረጃዎች በብቃት ተደራሽ እንዲሆኑና ለአለም አቀፍ ፤አገር አቀፍም ሆነ በክልል፤ ዞን፤ ወረዳና ቀበሌ ደረጃ የአመልድ ገጽታ ግንባታ እንዲጠናከር ማድረግ ነው፡፡

ይህንን አለማውን ዳር ለማድረስ የተለያዩ ማስፈጸሚያ ስለቶች ተቀርጸዋል የኮሙኒኬሽንና ሲስተሙን የአፈፃፀም መመሪያዎችን መቅረጽ፤ ወቅታዊ ግብረ መልስ ሊካሄድ የሚችልበት የኮሙኒኬሽንና ከባቢያዊ ሁኔታ መፍጠር፤ በሁሉም ዘንድ የሚታዎቅ ድርጅታዊ መለያ ተክለ አቋም እንዲጎናጸፍ ማድረግን ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ግንኙነቱን ማጠናከር ናቸው፡፡ ለእነዚህ ውጤታማነት ልዩ ልዩ ጥረቶች ያለመታከት በመካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

ሌላው አገልገሎቱ በዋነኝነት አንዲያተኩርና እንዲያሳካው የሚጠበቀው የአመልድን ፕሮግራሞች  እንቅስቃሴ ለመደገፍ የየሚችሉ ጠቃሚና ወቅታዊ መረጃዎች ተደራጅተው የሚገኙበት ለህዝብና ለአጋር አካላት የሚደርሱበትን ሁኔታዎች ማመቻቸት እንዲሁም ማረጋገጥ ነው፡፡

አመልድ ተረማጅ የክህሎት እውቀት መነሻ የሚሆን የመረጃ ቋትና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስርዓት እንዲፈጠር ይሻል፤ ይህም  የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ለአለም አቀፍ የዘርፉ እድገት ጋር ተጣጥሞ እንዲቀጥል ማድረግንም ያካትታል፡፡ ይህንኑ ፍላጎቱን ለማሳካትም አገልግሎቱ ከጂ አይ ኤስና ከኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ጋር ተዛማጅ የሆኑ ተግባራትን በማከናዎን ረገድ ሃላፊነቱን ለመወጣት እየታተረ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ከአመልድ መልቲሜዲያ ያገኛሉ!