Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ መምሪያ ውስጥ ኦዲትና ቁጥጥር

ውስጥ ኦዲትና ቁጥጥር

ከአመልድ ሰፊ የልማት እንቅስቃሴ አኳያ የሀብቱ ማለትም የገንዘብና ንብረት መጠኑን ከፍተኛ እንደሚሆን ይገመታል፡፡ በተለይም ከጥር 2004 እስከ ታህሳስ 2005 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ድርጅቱ 440.2 ሚሊዬን ብር ወይም 25.62 ሚሊዬን የአሜሪካን ዶላር ያህል አሰባስቧል፡፡

ሀብቱ ያላግባብ እንዳይባክና የግል ኪስ ማበልጸጊ እንዳይሆን አመልድ ገንዘብና ገንዘብ ነክ ያልሆኑ ንብረቶቹን በብቃት ጥቅም ላይ ለማዋልና የተዘረጉ ስርዓቶችና አሰራሮች በተገቢው ሁኔታ ተግባራዊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በትጋት እየታተረ ይገኛል፡፡

ለዚህም ድርጅቱ ተገቢ የማስፈጸሚያ ስልቶችን ቀርጾ ተግብሯል፤ የአካውንታንቶችን፣ የንብረት አስተዳደር ባለሙያዎችንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ሰራተኞች አቅም ገንብቷል፤ አመታዊ የሂሳብ ምርመራ በውጭ ኦዲተር ያለማቋረጥ ይካሄዳል፤ ስህተቶችንም ሆነ ተገቢ ያልሆነ አጠቃቀም ከመከሰቱ በፊት አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ቅድመ የሂሳብ ምርመራን አጠናክሯል፤ በተጨማሪም ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በሚደረሰው ስምምነት መሰረት ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉ እያደረገ ነው፡፡

በዚህ መሰረት በድርጅቱ ውስጥ ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሰፍን ሙያው የሚጠይቃቸውን መስፈርቶች እንዲያሟላ ተደርጎ የተደራጀው የውስጥ ኦዲትና ቁጥጥር ስርዓት ስራ ላይ ውሏል፡፡