የደን፤አካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም
- የተለያዩ የአፈር እና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን እና ስነ-ህይዎታዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የአፈር ለምነትን ማሻሻል እና ምርታማነትን ማሳደግ፣
- የደን ሽፋንን ለመጨመር የተለያዩ አገር በቀል እና የውጭ ዝርያ ዛፎችን መትከል፣
- የተፈጥሮ ደን መጨፍጨፍን መከላከል እና ብዛ-ህይወትን መመለስ፣ አሳታፊ የደን ልማት ማካሄድ፣
- ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ማህበረሰብ መፍጠር፣
- በገጠር አማራጭ የሃይል ምንጮችን ማቅረብ፣
- የአፈር እና ውሃ ጥበቃ፣ የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም እና የተፋሰስ ልማት ምርጥ ተሞክሮዎችን እና የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን ማስፋት፣