Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ አገልግሎቶች የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር

           የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር

የድርጅቱን ሠራተኞች የሙያና የአመራር ሰጨነት አቅም የክልሉ ህዝቦችና ተቋማቱ እንዲበቁና ሁለንተናዊ ችግሮቻቸውን በራሳቸው እንዲፈቱ የሚያደርጉትን ጥረት በሚያግዝ አኳኋን ማጎልበት የአመልድ የሰው ሀብት ልማትና አመራር ግብ ነው፡፡ 

ይህንን ግብ ለማሳካት የሚደረጉ ጥረቶች ድርጅቱ በአለም አቀፍ ለጋሾች ዘንድ ያለውን ተቀባይነት እንዲጨምር በማድረግ ረገድ የሰው ኃይሉ መተኪያ የሌለው ሃብቱ ሆኖ እንዲቀጥል ለማስቻል ቁልፍ ሚና ይጫወታል፡፡ ተወዳዳሪና የተሻለ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ማግኘት፣ የሠራተኞችን ክህሎት ማሳደግ፣ ወደላቀ የመፈጸም አቅም ደረጃ እንዲደርሱ ማነሳሳትና ረጅም ጊዜ ድርጅቱን በጽናት እያገለገለ እንዲቆዩ ማስቻል እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

ድርጅቱ የሰራተኛ ምልመላና ቅጥር፣ ደረጃ እድገት፣  ዝውውርና  ማትጊያ፣ የአቅም ግንባታ አፈጻጸምንና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን ያካተተ የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር መመሪያን ስራ ላይ ያዋለ ሲሆን በየጊዜውም እንዲሻሻል እያደረገ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት አመልድ ባሉት 819 (228ቱ ሴቶች) ሰራተኞች ውጤታማ እንቅስቃሴ እያካሄደ ነው፤  ከእነዚህ ውስጥ 184 (45ቱ ሴት) በዋናው መሥሪያ ቤት፣ 12 (7ቱ ሴ) በአዲስ አበባ የሀብት ማስባሰብና ግንኙነትና 623 (171ዱ ሴ) በወረዳ ደረጃ በሚገኙ የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የአመልድ ሠራተኞች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተግባብተው የሚሰሩ፣ ወግና ባህሉን የሚያከብሩ፣ ደስታውንና ችግሮቹን የሚጋሩና ለድርጅቱ ተግባራት መፈጸምና ለዓላማው መሳካት ቁርጠኛነትን የተላበሱ መሆናቸውን ለጋሾችንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ጨምሮ ከተለያዩ አጋር አካላት የተሰበሰቡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡