ለአካል ጉዳተኞች ማሳየት የሚገባን ጥሩ ባህሪያት

    Disability Etiquettes

አመልድ አካታችነትን ማዕከል አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ የአካል ጉዳተኞችን ችግር ለመቅረፍ ይሰራል፡፡ በመሆኑም ከአካል ጉዳተኞች ጋር በሚኖረን ማህበራዊ ግንኙነት ሁሉም የአመልድ ሰራተኞች፣ በጎ ፍቃደኞች እና አጋር ድርጅቶች የሚከተሉትን ጥሩ ባህሪያት ልንተገብር ይገባል፡፡ከማገዝ በፊት ፍላጎታቸውን መጠየቅ፡-

  1. ከማገዝ በፊት ፍላጎት እንዳለቸው መጠየቅ ይገባል፡፡ ሁሉም የአካል ጉዳተኞች ድጋፍ ላይፈልጉ ይችላሉ፡፡
  2. የአካል ንክኪ ላይ ጥንቃቄ ማድረግ፡- አንዳንድ አካል ጉዳተኞች እጃቸውን እንደሚዛን መጠበቂያ ሊጠቀሙ   ይችላሉ፡፡ ለመርዳትም ቢሆን መታከክ አይገባም፡፡ ተሸከርካሪ ወንበራቸውን እና ነጭ በትር መንካት      የለብንም፡፡
  3. ከመናገርህ በፊት ማሰብ፡- መናገር የምንፈልገውን ነገር ለኣጋዣቸው ከመናገር ይልቅ ቀጥታ ለእነርሱ    መንገር ይገባል፡፡
  4. ቀድሞ መፈረጅ አይገባም፡- የአካል ጉዳተኞች ህፃናት ካልሆኑ በስተቀር መስራት የሚገባቸውን እራሳቸው    እንዲወስኑ መተው እንጅ ቀድሞ መገደብ አይገባም፡፡
  5. በትኩረት መስማት፡-የመናገር ችግር ያለባቸው ሰዎችን ንግግር ማቋረጥ እና ስህተት መሆናቸውን    ለመግለፅ መቸኮል አይገባም፡፡ ሃሳባቸውን እንዲጨርሱ ማድረግ ይገባል፡፡
  6. የመናገር ችግር ያለባቸው ሰዎች ሃሳባቸው ግልፅ ካልሆነ እንዲደግሙት መጠየቅ ይገባል፡፡ዚህም    ሃሳባቸው ተቀባይነት እንዳለው ይሰማቸዋል፡፡
  7. አዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸው ሰዎች ጋር ስናወራ አጫጭር /ነገሮችን እና ግልፅ ቃላትን መጠቀም    ተገቢ ነው፡፡
  8. ማካተት፡- በሰዎች መካከል ንግግር/ጨዋታ ሲኖር የአካል ጉዳተኞች አይመቻቸውም ወይም አይመቹም      በማለት ማግለል አይገባም፡፡
  9. የተደበቁ የአካል ጉዳቶች፡- አንዳንድ ሰዎች በሌሎች ዘንድ በግልፅ የማይታወቁ የአካል ጉዳቶች ካሉባቸው    ስለአካል ጉዳታቸው ቀድሞ መፈረጅ  አይገባም፡
  10. ስለአካል ጉዳተኞች ማወቅ፡- ስለአካል ጉዳተኛነት በቂ መረጃ ሲኖር ተጨባጭ ያልሆኑ ፍርሃቶችን አስወግደን ሰዎችን እኩል ማየት እንችላለን፡፡