“አሁን በራስ መተማመን እና የህሊና መረጋጋት ይሰማኛል

         feel confidence

ብዙ ወጣቶች ትኩስ ጉልበት እያላቸው የስራ መስሪያ ገንዘብ ባለማግኘታቸው ወርቃማ የወጣትነት ጊዜያቸውን በአልባሌ ያሳልፋሉ፡፡ የወጣትነታቸው ጊዜ ካለፈ በኋላ እልህ እና ራዕያቸው በዚያው ልክ እየቀዘቀዘ ይሄዳል፡፡ ቀሪ ጊዜያቸውን ከእጅ ወደ አፍ ኑሮን እየተለማመዱ ዛሬን ኑሮ ለማለፍ ይሞክራሉ፡፡ በዚህም ለአገራቸው የሚጠበቅባቸውን ሃብት ባለመፍጠራቸው የእርጅና ጊዜ መጦሪያ ሳይዙ ይቀራሉ፡፡ አመልድ የክልሉ ወጣቶች የራሳቸውን የስራ እድል ፈጥረው አገራቸውን እንዲጠቅሙ በፕሮግራም ደረጃ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡

         feel confidence 1

በአመልድ የወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ፣ ስልጠና እና ድጋፍ ፕሮጀክት .. ከሃምሌ 2018 ጀምሮ ከጋፋት ኢንዶውመንት እና አመልድ በጋራ በተገኘ 5,245,696 ብር በጀት 200 ስራ-አጥ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ በደ/ጎንደር ዞን እብናት ወረዳ እየተተገበረ ነው፡፡ ከተጠቃሚዎች መካከል 23 ዓመቷ ወጣት ትዕግስት ምናለ አንዷ ናት፡፡ ላለፉት 7 ዓመታት በግል የውበት ሳሎኖች በወር 600 ብር እየተከፈላት ተቀጥራ ሰርታለች፡፡ የምታገኘው ገቢ ትዳር መስርቶ ኑሮ ለመምራት ግን በቂ አልነበረም፡፡ በዚህም በፕሮጀክቱ የቢዝነስ ፈጠራ እና የገንዘብ አያያዝ ስልጠና ካገኘች በኋላ የስራ ማስጀመሪያ 80 ሺህ ብር ብድር 8% ወለድ አግኝታ የራሷን የውበት ሳሎን ከፍታለች፡፡ የፕሮጀክቱን ብር ለወጣቶቹ በብድር የሚያቀርበው እና የሚያስተዳድረው የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ነው፡፡

በአመልድ ፕሮጀክት ስልጠና እና ብድር አግኝቼ ወደ ስራ የገባሁት በሰኔ 2011 . ነበር፡፡ 80 ሺህ ብር ለሶስት ዓመት 8% ወለድ ተበድሪያለሁ፡፡ በብድሩ ገንዘብ ለውበት ሳሎን የሚያስፈልገኝን መስሪያ እቃዎችን ገዝቻለሁ፡፡ ቤት በአንድ ሺህ ብር ተከራይቼ በሰኔ 2011 . ስራ ጀመርሁ፡፡ ገበያው ጥሩ ነው፡፡ አሁን በወር 5 ሺህ ብር አገኛለሁ፡፡ አንድ ረዳት ባለሙያ በአንድ ሺህ ብር ቀጥሬ እየሰራሁ ነው፡፡ የብድሬን የመጀመሪያ ስድስት ወር ክፍያ 14 ሺህ ብር መልሻለሁብላለች፡፡

አሁን በራስ መተማመን እና የህሊና መረጋጋት ይሰማኛል፡፡ የቢዝነስ ስራየን በማሳደግ ለአገሬ አንድ ነገር ማበርከት እንደምችል አርግጠኛ ነኝ፡፡