Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች ሁሉን አቀፍ የመሬት አያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ለተሻለ ምርታማነት!

ሁሉን አቀፍ የመሬት አያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ለተሻለ ምርታማነት!

     Comprehensive land husbandry 4

በተራራማ አካባቢዎች ላይ የሚደርሰውን የአፈር ክለት ለመከላከልና ለተራራማ አካባቢዎች ተስማሚ የሆኑ ሁሉን አቀፍ የመሬት አያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ከጥቂት ዓመታት በፊት ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል።

አመልድ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የመሬት አያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ ላይ በመስራቱ የሰብል ምርታማነትን አሳድጓል። በዚህ ረገድ አመልድ ኢትዮጵያ በአርአያነት ሊወሰዱ የሚችሉ ውጤቶችን አስመዝግቧል።

በአመልድ ኢትዮጵያ ወርልድ ቪዥን ኬር በጥምረት ሲተገበር የቆየው ተቋማትንና አይበገሬነትን ማጠናከር የምግብ ዋስትና ልማት ፕሮጀክት በተለይ የኑሮ ማሻሻያ፣ የጤና፣ ስርዓተ-ምግብ እና ስነ-ንፅህና፣ የአደጋ እና የአየር ንብረት ለውጥ ስጋትን መቆጣጠርን ጨምሮ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን ተጠቃሚ በማድረግ፣ ወጣቶችን በማብቃት ኑሯቸውን ማሻሻል ላይ አተኩሮ እኤአ ከመስከረም 30/ 2016 እስከ መስከረም 29/ 2021 ድረስ ሲሰራ ቆይቷል።

     Comprehensive land husbandry 2

የመሬት አያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂ በገጠር አካባቢ ያለውን ድህነት ለመቅረፍ በሚያስችል መልኩ ለምነታቸውን ያጡ ኮረብታማ/ተራራማ አካባቢዎችን ለምነታቸውን በመመለስ እና የተሻሻለ የግብርና ቴክኖሎጂን ለአርሶ አደሩ በማሳየት ምርታማነትን ማሳደግ ነው።

የአመልድ ስትራቴጂክ አጋር በሆነው የአሜሪካ የልማት ተራድኦ ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ሲሰራ የቆየው የግዘፍና ስነ-ህይወታዊ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን ጨምሮ ብዙ ጉልበት የሚጠይቁ የህዝብ ስራዎችን በመደገፍ ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

     Comprehensive land husbandry 3

ተፋሰስን መሰረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም

1. የተመናመነው የተፈጥሮ ሃብት ፈጥኖ እንዲያገግም ያስችላል

2. የአፈር ለምነት እንዲሻሻል በማድረግ ውሃ የመያዝ አቅሙን ያሳድጋል

3. የሰብል ምርታማነትን/የግብርና ምርታማነትን በመጨመር የአርሶ አደሩን ህይወት እንዲለውጥ ይረዳል

4. የመሬትና የውሃ ሃብትን በእንክብካቤ/በዘላቂ ሁኔታ መጠቀም የሚያስችልና ተጨማሪ የእርሻ መሬት እንዲፈጠር ያደርጋል

አመልድ ኢትዮጵያ በዳህና፣ ጋዝጊብላ፣ አይና ቡግና እና ሌሎች አካባቢዎች ተፋሰስን መሰረት ያደረገ ሁሉን አቀፍ የመሬት አያያዝና አጠቃቀም ቴክኖሎጂን በማስተዋወቅ ተሞክሮው እንዲስፋፋ ሲሰራ ቆይቷል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today0
Week68
All134762

Currently are 73 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?