Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች አካል ጉዳኝነትና የአዕምሮ እድገት ውስንነት የሃጢያት/እርግማን ውጤት አይደለም

   አካል ጉዳኝነትና የአዕምሮ እድገት ውስንነት የሃጢያት/እርግማን ውጤት አይደለም

     Disability and 2

አቶ ደስታው ትዳር መስርተው ልጆችን ወልደው፣ እንደአካባቢያቸው ባህል እና ወግ ይኖራሉ፡፡ ከዚህ ሁሉ ግን አንድ ነገር የቤተሰባቸው ቆየ ችግር እንዳለባቸው ያወራሉ፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸው ከማህጸን ጀምሮ የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለበት እና በእግሩ ራሱን ችሎ መራመድ አይችልም፡፡ በዚህም ልጃቸው ላፉት 19 ዓመታት እንደእኩዮቹ መጫወት፣ መማር እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ላይ መሳተፍ አልቻለም፡፡

አቶ ደስታው ነጋ በደቡብ ጎንደር ዞን፣ ጉና በጌምድር ወረዳ፣ የውቅሮ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ 45 ዓመት ጎልማሳ፣ ባለትዳር እና 4 ልጆች አባት ናቸው፡፡ መተዳደሪያቸው የግብርና ስራ ሲሆን ሁለት በሬ፣ አንድ ላም እና 0.375 ሄክታር (3 ጥማድ) መሬት አላቸው፡፡ እንዲሁም ኑሯቸውን ለመደጎም በግ በማርባት እና የተለያዩ ሰብሎችን በአህያ እየጫኑ በችርቻሮ ይነግዳሉ፡፡ ባለቤታቸው እና 3 ልጆቻቸው በግብርና ስራው ያግዟቸዋል፡፡ የመጀመሪያ ልጃቸው ወጣት ወርቁ ግን አካል ጉዳት ያለበት በመሆኑ የቤተሰቡን ልዩ እገዛ እና ክትትል ይፈልጋል፡፡ ወላጆቹም የወደፊት የልጃቸውን እጣፋንታ ሲያስቡ አብዝተው ይጨነቁ ነበር፡፡

     Disability and 1

በአመልድ ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የጤና፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ልማት ፕሮጀክት በሆፕ ኤንድ ሂሊንግ ኢንተርናሽናል የገንዘብ ድጋፍ የልጃገረዶችን እና የወጣቶችን ህይዎት ለማሻሻል እና ለትራኮማ ተጠቂ የሆኑ እና የአካል ጉዳት ያለባቸው ቤተሰቦችን ኑሮ ለማሻሻል በውቅሮ ቀበሌ እየሰራ ይገኛል፡፡ አቶ ደስታውም የቤተሰባቸው አባል የሆነው የመጀመሪያ ልጃቸው የአካል ጉዳተኛ በመሆኑ የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ፕሮጀክቱ የአካል ጉዳተኛ ልጃቸውን ህይዎት እና የቤተሰቡን ህይዎት ለማሻሻል በእሴት ሰንሰለቶች እንዲሳተፉ ማለትም በበግ ማርባት እና የአካል ጉተኞች እራሳችን እንዲችሉ ለማድረግ ስልጠና ሰጥቷቸዋል፡፡ በዚህም 2012 . ሁለት እናት በግ እና አንድ አውራ በግ በድጋፍ አግኝተው ባለፉት 2 ዓመታት በበግ እርባታ ተጠቃሚ ሁነዋል፡፡

ከፕሮጀክቱ በሰጠኝ እናት በጎችን በማርባት ተጠቃሚ ነኝ፡፡ ባለፈው ዓመት 2 የተወለዱ ጠቦቶችን 1ሺህ 300 እና 1ሺህ 200 ብር በመሸጥ የአፈር ማደበሪያ ገዝቻለሁ፡፡ ዘንድሮ ደግሞ 2 ግልገል በጎችን 2ሺህ 100 እና 1ሺህ 350 በመሸጥ ባገኘሁት ገቢ ለወርቁ አንድ ጥጃ ለመግዛት በሂደት ላይ ነኝ፡፡ብሏል፡፡ አቶ ደስታው አሁን በአጠቀላይ 4 እናት በግ እና 2 ግልገል በጎች አሉት፡፡

አቶ ደስታው የአካል ጉዳተኛ የልጃቸውን ህይዎት ለማሻሻል ለተደረገላቸው ድጋፍ ፕሮጀክቱን የሚተገብረውን አመልድ ኢትዮጵያ እና በገንዘብ የሚደግፈውን ሆፕ ኤንድ ሂሊንግ ኢንተርናሽናልን አመስግነው፤ የአካል ጉዳተኛ ልጃቸው የመንቀሳቀሻ ዊልቸር እና የልዩ ፍላጎት ትምህርት ቢያገኝ ደስታቸው ወደር እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

የአካባቢው ማኅበረሰብ የአካል ጉዳተኛና የአዕምሮ እድገት ውስንነት ያለባቸውን ወገኖች በፈጣሪ ቁጣ የመጣ እና የተረገሙ አድርጎ የማ/ሰቡ ባህልም እንዲቀረፍ ፕሮጀክቱ መልካም ስራ ሰርቷል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today54
Week200
All97949

Currently are 4 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?