Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች አመልድ ኢትዮጵያ

አመልድ ኢትዮጵያ

      ORDAethiopiaam

                           በትብብር ለውጥ ማምጣት

አመልድ ኢትዮጵያ መንግስታዊ ያልሆነና ለትርፍ ያልተቋቋመ አገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡እ.ኤ.አ በ1991 አገር በቀል ድርጅት ሆኖ በኢትዮጵያ የአደጋ ጊዜ ማቋቋም ኮሚሽን የተመዘገበ ሲሆን በድጋሚእ.ኤ.አ በ1999 በፌደራል ፍትህ ሚኒስቴር ተመዝግቧል፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ በአዲሱ የበጎ አድራጎት እና ማህበራት አዋጅ መሰረት በአገር በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅትነት እ.ኤ.አ በ2009 በፈቃድ ቁጥር 0607 ተመዝግቧል፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያዊያን የተቋቋመ አትራፊ ያልሆነ እና መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን እ.ኤ.አ ከ1984 ጀምሮ ስር የሰደደውን ድህነት እና ረሃብን ለማስወገድ ስትራቴጂ ነድፎ በአካባቢ እና ደን ልማት፣በግብርና፣በሥነ-ምግብ፣በንጹህ መጠጥ ውኃ እና መስኖ ልማት ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡ ድርጅቱ 4.5 ሚሊዮን ተጠቃሚዎችን ለመድረስ ሰፊ ፕሮግራሞችን እና ስትራቴጅዎችን ነድፎ እየተንቀሳቀሰ ነው፡፡ ላለፉት ዓመታት ካካበተው ከፍተኛ የሥራ ልምድ፣ ዕውቀት እና ተከታታይ ስኬቶች በመነሳት 5ኛውን የስትራቴጅክ እቅዱን (እ.ኤ.አ 2021- 2025) አዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ገብቷል፡፡አራተኛው የስትራቴጂክ እቅድ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ተከትሎ በአለም አቀፍ ደረጃ የገንዘብ ረጂ ድርጅቶች ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች እና የሀብት ማሰባሰብ ውድድር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ከህብረተሰቡ ያልተሟሉ የልማት ፍላጎቶች ጋር ተዳምሮ አመልድ ኢትዮጵያ አምስተኛውን ስትራቴጂክ እቅድለማዘጋጀት ችሏል። ስለሆነም ይህ ስትራቴጂክ እቅድ ውጤታማ የሀብት ማሰባሰብን ለመምራት እንደ ማኔጅመንት መሳሪያ ሆኖ ያገለግላል፣ ከመንግስት ጋር ጠንካራ ትብብርን ይፈጥራል፣ ሃብትን በብቃት ለመጠቀም ይረዳል፣ የሕብረተሰቡን አቅም ያሳድጋል፣ ተጠያቂነትን እና የሥራ ጥራትን ለማምጣት ይረዳል፣ ጠንካራ የሥራ መንፈስ ይገነባል፤ በመጨረሻምየድርጅቱንየሥራ አፈጻጸም ውጤታማ በማድረግ የተጠቃሚዎችን ሕይወት ለመለወጥ ያስችላል፡፡

ድርጅቱ በደን ልማት፣ የአርሶ አደሩን ምርታማነት የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማቅረብ፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ የግልና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅ እና ትራኮማን በመከላከል፣ አነስተኛ የመስኖ አውታርዝርጋታ፣ አመጋገብን በማሻሻል እና መቀንጨርን በመከላከል በኩል ትልቅ ሚና ተጫውቷል።

የሚከተሉትን 5 ዋና ዋና ፕሮግራሞች በመላው ኢትዮጵያ ይተገበራሉ፤እነርሱም

     1. የደን፣ አካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም፣

     2. የውኃ፣ ሥነ-ንጽህና እና መስኖ ልማት ፕሮግራም፣

     3. የግብርና እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፕሮግራም፣

     4. የሥርዓተ-ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት አካታችነት እና የወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም

         .የምግብ እህል አስተዳደር እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራም ናቸው፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ ራዕይ፣ ተልዕኮ እና እሴቶች

የአመልድ ኢትዮጵያራዕይ

አስተማማኝ የልማት አጋርና በኢትዮጵያ የለውጥ አመቻ ችሆኖ ማየት

የጋራ ራዕይ

 • የበለጸገ የኢትዮጵያ ህዝብ ማየት

ተልዕኮ

 • በኢትዮጵያ የህብረተሰቡንና ተቋማትን አቅም በማሳደግ የኑሮ ዋስትናንና የአካባቢ ደህንነትን ማረጋገጥ

እሴቶች

 • የህዝብ አገልጋይነት፣ ሐቀኝነት፣ፅናት፣ግልፅነት፣ተጠያቂነት፣አካታችነት እና ሙያዊ ብቃት

የአመልድ ኢትዮጵያ ዓላማዎች

   1. የተቋማትን የመፈጸም አቅም ማጠናከር

   2. ቀጣይነት ያለው የተፈጥሮ ሐብት አያያዝን ማበረታታት

    3የተጠቃሚዎችን ኑሮ እንዲሻሻል ማገዝ

    4የተጠቃሚ ቤተሰቦችአመጋገባቸውን እንዲያሻሽሉ ማድረግ

    5ማህበረሰቦችን የንጹህ ውኃ ተጠቃሚ ማድረግ

    6የሴቶችን፣የአካል ጉዳተኞችን እና ወጣቶችን ተሳትፎ ማሳደግ

    7የምግብ ዋስትና ችግር ላለባቸው ዜጎች ድጋፍ ማድረግ ናቸው፡፡

   የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዋና ፕሮግራሞች

 1. የደን፣ አካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም 

•የተለያዩ የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ስራዎችን እናሥነ-ህይዎታዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የአፈር ለምነትን ማሻሻል እና ምርታማነትን ማሳደግ፣

•የደን ሽፋንን ለመጨመር የተለያዩ አገር በቀል እና የውጭ ዝርያ ዛፎችን መትከል፣

•የተፈጥሮ ደን መጨፍጨፍን መከላከል እና ብዛ-ህይወትን መመለስ፣ አሳታፊ የደን ልማት ማካሄድ፣

•ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ማሕበረሰብ መፍጠር፣

•በገጠር አማራጭ የሐይል ምንጮችን ማቅረብ፣

•የአፈር እና ውኃ ጥበቃ፣ የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም እና የተፋሰስ ልማት ምርጥ ተሞክሮዎችን እና የአሰራር ቴክኖሎጂዎችን ማስፋት፣

2. የውኃ፣ ሥነ-ንጽህና እና መስኖ ልማት ፕሮግራም

 • የንጹህ ውኃ ግንባታ ማካሄድ፣ የሥነ-ንጽህና መሻሻል ማምጣት፣ የመስኖ ልማት ግንባታ፣ የምንጭ ማጎልበት ሥራዎች እና የውኃ እቀባ ቴክኖሎጂዎችን ማስተዋወቅ፣
 • የአለም ጤና ድርጅት መርህ በመከተል ትራኮማን መከላከል እና መቆጣጠር፣
 • የማሕበራዊ መገልገያ ተቋማትን ማለትም መንገዶችን፣ድልድዮችን፣ ት/ቤቶችን፣ጤና ጣቢያዎችን፣ የእንስሳት ጤና ክሊኒኮችን፣ ወዘተ መገንባት እና ጥገና ማድረግ፣
 3.ግብርናሥርዓተ-ምግብ እና የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ፕሮግራም

• ፕሮግራሙ በጓሮ አትክልት ልማት፣ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ማስተዋወቅ፣የገበያ ትስስር መፍጠር እና በእንስሳት ልማት ዘርፍ ማለትም በዶሮ እርባታ፣በንብ ማነብ እና የመኖ ልማት ላይ አተኩሮ ይሰራል፡፡

• የመንደር ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ቁጠባን በማስተዋወቅ የአርሶ አደሩን የቁጠባ ልምድ ማዳበር፣

• የህፃናትን መቀንጨር ለመከላከል እና የእናቶችን ጤና ለመጠበቅ የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ይሰራል፣

4. የሥርዓተ-ጾታ፣ አካል ጉዳተኝነት አካታችነት እና የወጣቶች ሥራ-ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም

 • የሥርዓተ-ጾታ፣አካል ጉዳተኝነት አካታችነት እና ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል በዋና ዋና ፕሮግራሞች ተካትተው እንዲሰሩ ማድረግ፣ በዚህም እኩል ተጠቃሚነትን ያሰፍናል፡፡
 • በሁሉም የልማት ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች ውስጥ የሥርዓተ-ጾታ እና የአካል ጉዳተኝነትን ማካተት፣ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን እና ተሳትፎን ለማረጋገጥ ያግዛል፡፡
 • ፕሮግራሙ ወጣቶች የራሳቸውን የሥራ እድል እንዲፈጥሩ ማገዝ እና የግሉ ዘርፍ እንዲጠናከር ማድረግ፣
 5. የምግብ እህል አስተዳደር እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራም

• በምግብ ራሳቸውን ላልቻሉ ወገኖች እና ለአደጋ የተጋለጡ ማሕበረሰቦች የዕለት ምግብ እርዳታ ማድረግና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ማከናወን፤

የአመልድ ኢትዮጵያ አስተዋፅኦ (እ.ኤ.አ1984 - 2020)

አመልድ ኢትዮጵያ ላለፉት 38 ዓመታት (እ.ኤ.አ 1984-2021) ለማሕበረሰብ ልማት ማለትም ለኑሮ መሻሻል፣ ጤና አጠባበቅ፣ ንጽህና እና ሥነ-ንጽህና፣ የአካባቢ ልማት እና ጥበቃ ላይ ትልቅ ሚና ሲጫወት ቆይቷል።

ከ774.87 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በማፍላት በ132ሺህ 598 ሄክታር ማሳ ላይ 720.36 ሚሊዮን (44.12 አገር በቀል ችግኖች) ችግኖችን ተክሏል፡፡ በዚህም ምክንያት አመልድ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2007 የአረንጓዴ ሽልማት አሸናፊ ሁኗል፡፡እስካሁን ድረስ አንድ ሺህ 320 የማሕበረሰብ ተፋሰሶች ለምተዋል፡፡

ድርጅቱ እ.ኤ.አ ከ1997 ጀምሮ ላለፉት 24 ዓመታት 6 ሺህ 61 ንጹህ የመጠጥ ውኃ ተቋማትን በመገንባት 2.6 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ አድርጓል።በመሆኑም አመልድ ኢትዮጵያ በ2009 ዓ.ም በጽዳት እና ሥነ-ንጽህና በአገር አቀፍ ደረጃ ተሸላሚ ነበር፡፡ በተጨማሪም 51ሺህ 700 አባውራዎችን ተጠቃሚ ያደረጉ እና 13 ሺህ ሄክታር ማሳ ማልማት የሚያስችሉ 261 አነስተኛ መስኖዎችን ገንብቶ ለአርሶ አደሮች አስረክቧል፡፡

የአርሶ አደሮችን ሰብል ምርታማነት ለማሳደግ የተለያዩ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ሲያቀርብ ቆይቷል፡፡ በአጠቃላይ 27ሺህ489 ኩንታል የእህል ዝርያዎችንና 337ኩንታል የአትክልት ዝርያዎችን ለ186ሺህ 868 አርሶ አደሮች አሰራጭቷል፡፡ እንዲሁም 671,436 (ሴ፡324,215) ወጣቶችን በመንደር ኢኮኖሚያዊ ማህበራዊ ቁጠባ ቡድን በማደራጀት 74 ሚሊዮን 406ሺህ 344 ብር ቆጥበዋል፡፡

ከዚህ በዘለለ የአደጋ ስጋት እና የእለት ምግብ እርዳታዎችን ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህም 188ሺህ 635 ሜትሪክ ቶን ምግብ (ስንዴ፣የተከካ አተር እና የምግብ ዘይት) ለ256ሺህ 329 በከፍተኛ ሁኔታ ለምግብ እጦት ለተጋለጡ ዜጎች እና ለ753ሺህ 588 ለድንገተኛ አደጋ ተጋላጭ አርሶ አደሮች ተሰራጭቷል፡፡

የተቋማት አጋርነት

የማበረሰቦችንኑሮ በማሻሻል እናተቋሞቻቸውን በማብቃት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና የአካባቢ ደህንነትን ለማስፈን፤ አመል ድኢትዮጵያ ከመንግስት ባለድርሻ አካላት፣ ከሲቪክ ማህበራት እና ከማሕበረሰብ አቀፍ ድርጅቶች ጋር አጋርነት ይሰራል። አጋርነት የማሕበረሰብን የመልማት ጥያቄ ለመመለስ እና ቀጣይነት ያለው ለውጥ ለማምጣት ይረዳል፡፡ በዚህም የተጠቃሚዎችን ኑሮ ለማሻሻል እና አዎንታዊ ለውጥ ለማምጣት የአጋራትን ሚና አመልድ ኢትዮጵያ በቅጡ ተረድቷል፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ ዓላማዎች

1. የደን፣ የማሕበረሰብ ተፋሰስ ሥራዎችን፣ የብዛሃ ህይዎትንና አማራጭ ሐይልን በማስፋት እና በማጠናከር ለዘላቂ እና አረንጓዴ መር ልማት አስተዋጽኦ ማድረግ፣

2. የግብርና ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እና ከግብርና ውጭ ያሉ የገቢ ማስገኛዎችን በማስፋፋት የተጠቃሚውን ማሕበረሰብ ገቢ ማሳደግ እና ሥርዓተ-ምግብን ማሻሻል፣

3. የንጹህ መጠጥ ውኃ ተደራሽነትን፣ የግል እና የአካባቢ ንጽህናን በማስፋፋት፣ የትራኮማ እና ሌሎች ውኃ ወለድ በሽታዎችን በመቀነስ እንዲሁም ልዩልዩ የመስኖ ቴክኖሎጅዎችን በመተግበር የግብርናውን ዘርፍ ደረጃ በደረጃ ከዝናብ ጥገኝነት ማላቀቅ፣

4. በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ምክንያት በሚያጋጥሙ ቀውሶች ምግብ እና ምግብነክ ያልሆኑ ቁሶችን በማቅረብ የማህበረሰቡ እሴት እንዳይሟጠጥ እና ለስደት ወይም በምግብ እጦት ምክንያት ለከፋ ስቃይ እንዳይጋለጥ ማድረግ፣

5. የሥርዓተ-ጾታ እኩልነት እና የሴቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችንና ወጣቶችን የልማት ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፣

የአመልድ ኢትዮጵያ ሽልማቶች

አመልድ ኢትዮጵያ ባከናወናቸው ተግባራት በሀገር አቀፍ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝቷል።ድርጅቱ በአረንጓዴ ልማት እና በሥነ-ንጽህና ትግበራ (እ.ኤ.አ በ2007፣ 2009 እና 2015 ብሔራዊ እና ክልላዊ ሽልማቶችን ተቀብሏል)፡፡

በፕሮግራሙ በውጤታማነት እናጥራት እውቅና ያገኘባቸው ሽልማቶች፡-

 • አራተኛውን እና ስድስተኛውን የኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት (EQA) በሚያዚያ እ.ኤ.አ 2016 እና በጥር 2019 አግኝቷል።
 • ‘ESQR’ የጥራት ምርጫ ሽልማት እ.ኤ.አ በ2016 በርሊን፣ ጀርመን።
 • "The American BIZZ 2017" በአሜሪካ አገር፣
 • ዓለምአቀፍ 'ስኬቶችፎረም 2017' ለንደን፣ዩኬ ናቸው፡፡

በአሁኑ ወቅት አመልድ ኢትዮጵያ በከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ የሕብረተሰብ ክፍሎች ህይወት ላይ ለውጥ ለማምጣት በትኩረት እየሰራ ሲሆን የመንግስት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህበራት እና አጋር ድርጅቶች ለላቀ ስኬት በቅንጅት እንዲሰሩ ጥሪውን ያቀርባል።

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today57
Week233
All100762

Currently are 7 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?