Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች ድርጅቱ ከኦክስፋም ፣ ዌልት ሁንገር ሂልፈ እና ሄልቬታስ ያገኘውን 43.9 ሚሊዮን ብር ለተፈናይ ወገኖች ድጋፍ ሊያደርግ ነው !

ድርጅቱ ከኦክስፋም ዌልት ሁንገር ሂልፈ እና ሄልቬታስ ያገኘውን 43.9 ሚሊዮን ብር ለተፈናይ ወገኖች ድጋፍ ሊያደርግ ነው !

    Oxfam GB Welthungerhilfe and Helvetas

አመልድ ኢትዮጵያ ከዌልት ሁንገር ሂልፈ እና ሄልቬታስ 10 ሚሊዮን 276 ሺህ 7 መቶ ብር ድጋፍ አገኘ

ይህ ድጋፍ ከዋግኸምራ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ተፈናቅለው በዳህና ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ላይ ለሰፈሩ 5 ሺህ 755 ተፈናቃዮች በተለይ ነፍሰ-ጡሮች፣ አጥቢ እናቶች፣ ወላጅ አልባ ህጻናት፣ አረጋዊያን፣ በበሽታ ለሚሰቃዩ ወገኖች የተለያዩ ቁሳቁሶችን እያደረሰ ነው፡፡

    Oxfam GB Welthungerhilfe and Helvetas1

1 ሺህ 350 ብርድ ልብስ፣ የመመገቢያ ፕላስቲክ ሳህን፣ የሻይ በራድ፣ ብረት ድስት፣ የውሃ ባልዲ፣ የውሃ ጆግ፣ የንጽህና መጠበቂያ ሳሞና ለማድረስ እየተጓጓዘ ነው፡፡

በተጨማሪም 6.9 ሚሊዮን ብር ኃብት ንብረታቸው ለወደመ 5 ሺህ 755 ተፈናቃዮች ለእያንዳንዳቸው በካሽ 1 ሺህ 2 መቶ ብር ድጋፍ ይደረጋል፡፡

    Oxfam GB Welthungerhilfe and Helvetas3

በተመሳሳይ መልኩ ድርጅቱ ከኦክስፋም ባገኘው 33 ሚሊዮን 647 ሺህ ብር የተፈናቀሉ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ እየሰራ ነው፡፡ እርዳታው በደባርቅ፣ ደብረ ብርሃንና እብናት ጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች የውሃ ማጠራቀሚያ ሮቶ (6) የውሃ ቱቦ ማራዘሚያ (1 ሺህ ሜትር) መጸዳጃ ቤት (10 ብሎክ) የገላ መታጠቢያ/ሻወር/ ክፍሎች ((10 ብሎክ) የእጅ መታጠቢያ (8) የቆሻሻ ማስወጃ (8) 20 ሊትር የሚይዝ ጀሪካን፣ የልብስ ማጠቢያ ሳፋና የውሃ ባልዲ እያንዳንዳቸው 1 ሺህ 6 መቶ፣ የልብስና የገላ ሳሞና፣ ባትሪ፣ የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ እና የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለማድረስ እየሰራ ነው፡፡

ከዚህ ባሻገር 10 ሚሊዮን 395 ሺህ ብር ኃብት ንብረታቸው ለወደመ 1 ሺህ 155 ተፈናቃዮች ለእያንዳንዳቸው በካሽ ብር 3 ሺህ ብር 3 ተከታታይ ወራት ድጋፍ ይደረጋል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today22
Week344
All86765

Currently are 20 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?