Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች ግብርናን ከተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ እና ከስነ-ምግብ ፕላስ ጋር የማስተባበር ፕሮጀክት የአርሶ አደሮችን ህይዎት የሚቀይሩ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወኑ ተገለፀ

ግብርናን ከተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ እና ከስነ-ምግብ ፕላስ ጋር የማስተባበር ፕሮጀክት የአርሶ አደሮችን ህይዎት የሚቀይሩ ውጤታማ ሥራዎችን ማከናወኑ ተገለፀ

    Nutrition-PLUS LANN

አመልድ ኢትዮጵያ ግብርናን ከተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ እና ከስነ-ምግብ ፕላስ ጋር የማስተባበር ፕሮጀክት በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት ወረዳዎች ማለትም በጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ 3 ቀበሌዎች (ደብረ ሃይል፣የቡቻር እና የቡዛ ) እንዲሁም እናርጅ እናውጋ ወረዳ 3 ቀበሌዎች (የጎሳ፣ታሞ ዳዋሮ እና ጥጣር ባድማ) በድምሩ 36 ሺህ 500 ነዋሪዎችን በስነ-ምግብ እና ስነ-ፅዳት ዙሪያ የባህሪ ለውጥ እና መሻሻል እንዲያመጡ እየሰራ ይገኛል፡፡

     Nutrition-PLUS LANN 1

ፕሮጀክቱ አርሶ አደሮች በጓሮ አትክልት ልማት፣ በበግ እርባታ እንዲሳተፉ በማድረግ እና ንጹህ መጠጥ ውኃ በመገንባት ተጠቃሚ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ አስማረ እንዳሉት ላለፈው አንድ ዓመት የጓሮ አትክልት ለማልማት የሚያስችሉ 443 የገመድ ውኃ መሳቢያ ፓምፖች በአርሶ አደሮች ጓሮ ተገንብተው የጓሮ አትክልት እንዲያለሙ ተደርርጓል፡፡ አርሶ አደሮች ምርታማ እንዲሆኑ 525.25 ኩንታል ምርጥ የስንዴ ዘር እና 6.25 ምርጥ የቦቆሎ ዘር፣ 59 . የአትክልት ዘር፣ 10ሺህ በላይ የፍራፍሬ ፍግኞች አቅርቧል፡፡ እንዲሁም 9 መለስተኛ ጥልቅ ንጹህ መጠጥ ውኃ ጉድጓዶችን እና የምንጭ ማጎልበት ሰርቶ ተጠቃሚዎች ንፁህ መጠጥ እንዲያገኙ አድርጓል፤ 100 ምርታማ የዋሸራ አውራ በግ በመስጠት 839 ጠቦቶች ተወልደዋል፡፡ በተጨማሪም ተጠቃሚዎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ 2ሺህ (ሴ፡794) አርሶ አደሮች 10ሺህ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን አከፋፍሏል፡፡

     Nutrition-PLUS LANN 3

ፕሮጀከቱ ከቬልት ሁንገር ሂልፈ (welt hunger hilfe 75%) እና ከአማራ ክልል መንግስት በተገኘ የእርዳታ ማሟያ ገንዘብን (matching fund 25%) ጨምሮ 2 ሚሊዮን ዩሮ 2012 . ወደ ትግበራ መግባቱ ይታወሳል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today28
Week350
All86771

Currently are 23 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?