አመልድ ኢትዮጵያ በባህር ዳር ዘንዘልማ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገ

     Bahir Dar IDP Center1

በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው ዘንዘልማ የተፈናቃይ ካምፕ ከሰሜን ወሎ እና ዋግþምራ ዞን ጦርነቱን ሸሽተው የመጡ በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች ይገኛሉ፡፡ ተፈናቃዮች የእለት ምግብ፣አልባሳት እና የንጹህ መጠጥ ውኃ በበቂ ሁኔታ የሚያስፈልጋቸው መሆኑ ይታመናል፡፡ በዚህም አመልድ ኢትዮጵያ ከሲአርኤስ ጋር በመሆን በባሕር ዳር ከተማ እና ዙሪያው ተጠልለው ለሚገኙ 33 ሺህ ተፈናቃዮች የእለት ደራሽ እርዳታ ማለትም 4ሺህ 950 ኩንታል ስንዴ፣ 495 ኩንታል ክክ እና 14ሺህ 850 ሊትር የምግብ ዘይት ለማሰራጨት እየሰራ ይገኛል፡፡ ከዚህም ውስጥ 11 ሺህ 191 ዘንዘልማ ለሚገኙት ተፈናቃዮች በዓይነት ማለትም 1ሺህ 678.65 ኩንታል ስንዴ፣ 167.865 ኩንታል የተከካ አተር እና 5,035.95 ሊትር የምግብ ዘይት ተሰራጭቷል፡፡

      Bahir Dar IDP Center