Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በጦርነት ምክንያት ለተፈናቃሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ ለአሜሪካ አምባሳደር ገለፃ አደረጉ

የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር በጦርነት ምክንያት ለተፈናቃሉ ዜጎች ሰብዓዊ ድጋፍ በሚደረግበት ዙሪያ ለአሜሪካ አምባሳደር ገለፃ አደረጉ

     Executive Director briefs US Ambassador

በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰውን ግጭት በመሸሽ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች በስደተኛ መጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በተለይም በአማራ ክልል ዋግኽምራ፣ ሰሜን ወሎ፣   ደቡብ ወሎ እና ሰሜን ጎንደር ዞን (ከጠለምትና አዳርቃይ ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ ተጠልለው የሚገኙትን ጨምሮ) በመቶ የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች በደሴ፣ በባሕር ዳር፣ በኮምቦልቻ፣ በደባርቅ እና ሌሎች ከተሞች ላይ በትምህርት ቤቶች እና በጊዚያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ተጠልለው ለማህበራዊ ቀውስ ተዳርገዋል፡፡

     Executive Director briefs US Ambassador 1

በዚህም ተፈናቃዮች የዕለት ምግብ፣ መድሃኒት፣ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን እያገኙ አይደለም፡፡ በመሆኑም በጉብኝቱ ወቅት የአመልድ ዋና ዳይሬክተር / ዓለማየሁ ዋሴ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ የተመራ የልኡካን ቡድንን፣ በአሜሪካን የልማት ተራድኦ ድርጅት ኤስ ኤይድ የሰብዓዊ እርዳታ ጉዳዮች ቢሮ ረዳት አስተዳዳሪ፣ የኢትዮጵያ ሚሽን ዳይሬክተር ሺያን ጆንስ ለተፈናቃዮች መሠረታዊ ፍላጎቶችን በጋራ ለማድረስ በሚያስችልበት ሁኔታ ላይ ጥቅምት 12/ 2014 . በባሕር ዳር ውይይት አድርገዋል፡፡ / ዓለማየሁ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በአማራ ክልል ላለፉት 20 ዓመታት ላደረገው ድጋፍ አመስግነው ነገር ግን አሁን ላይ በአማራ ክልል በጦርነት ተፈናቅለው በስደተኛ ጣቢያ ላሉ ወገኖች የዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች ያሳዩት ድጋፍ አነስተኛ እና የዘገየ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

      Executive Director briefs US Ambassador 2

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፓሲ በበኩላቸው በሰሜን ኢትዮጵያ በጦርነት ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ያለምንም አድልኦ የዕለት እርዳታ ለማቀረብ የቻልነውን ሁሉ እናደርጋለን ብለዋል፡፡ በጉብኝቱ አምባሳደር ፓሲ በባሕር ዳር ዘንዘልማ የስደተኞች ጣቢያ ከመጡ ተፈናቃዮች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡

     Executive Director briefs US Ambassador 3

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today61
Week155
All83649

Currently are 29 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?