Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች የጽዱ አካባቢ ተምሳሌት የሆነችው የገዳማዊት ቀበሌ

     የጽዱ አካባቢ ተምሳሌት የሆነችው የገዳማዊት ቀበሌ

     Gedamawit Kebele

የግል ንፅህና ችግር እና በሜዳ ላይ መፀዳዳት በማህበረሰብ ላይ አሉታዊ የጤና እና ሌሎች ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ያስከትላሉ፡፡ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በኢትዮጵያ የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም አሁንም ቢሆን ዝቅተኛ ነው፡፡ የአለም ጤና ድርጅት ሪፖርት እንደሚያሳየው በኢትዮጵያ የተሻሻለ መፀዳጃ ቤት የሚጠቀሙ ሰዎች 63 በመቶ ሲሆኑ ቀሪ 37 በመቶዎች በሜዳ ላይ ይፀዳዳሉ፡፡ በዚህም በአመልድ ኢትዮጵያ ጆን ሪግ ዋሽ ፕሮጀክት በምስራቅ ጎጃም ዞን 5 ወረዳዎች የውሃ ተቋም ግንባታ የንፅህና እና ስነ-ንፅህና ተግባራት ላይ እየሰራ ይገኛል፡፡ በቪቫ ኮን አግዋ በኩል ከቬልት ሁንገር ሂልፈ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአጠቃላይ 8.8 ሚሊዮን ፓውንድ በጀት መድቦ 2016 . ጀምሮ በጎዛምን ማቻከል ደብረ-ኤልያስ አነደድ እና ስናን ወረዳዎች ላይ 205 ህዝብ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ እና 280ሺህ ህዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ የስነ-ንፅህና እና የአካባቢ ብክለት መከላከል ስራዎችን እየሰራ ነው፡፡

ፕሮጀክቱ ውጤታማ የግል እና የአከባቢ ንፅህና አጠባበቅ ስራ ከሰራባቸው ቀበሌዎች መካከል በስናን ወረዳ የገዳማዊት ቀበሌ አንዱ ነው፡፡ በቀበሌው ተጠቃሚዎችን በአንድ 30 በማደራጀት የግል ንፅህናን እና የአካባቢን ንፅህና ለመጠበቅ የሚያስችል ስልጠና እና የአባላት ወርሃዊ የመማማር ፕሮግራም በማዘጋጀት ተጨባጭ ለውጥ አምጥቷል፡፡ በዚህም የቀበሌዋ ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ንፅህና እና የግል ንፅህናቸውን ለመጠበቅ የተሻሻሉ መፀዳጃ ቤቶችን፣ ሻወር ቤቶችን እና የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ስርዓቶችን ገንብተዋል፤ የውሃ ማጣሪያ ቱሊፕ ገዝተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን በስነ-ንፅህና ዙሪያ በማሰልጠን፣ በመከታተል እና የተሻለ አፈፃፀም ያመጡትን ደግሞ በመሸለም ፅዱ አካባቢን ለመፍጠር ተችሏል፡፡

     Gedamawit Kebele1

ከተጠቃሚዎች መካከል በስናን ወረዳ ገዳማዊት ቀበሌ ነዋሪ / ማስተዋል ሽቴ አንዷ ሲሆኑ ባለትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ናቸው፡፡ በፕሮጀክቱ ታቅፈው የአካባቢ እና የግል ንፅህናን ለመጠበቅ የሚረዱ ስልጠናዎችን አግኝተዋል፡፡ ባለቸው ንቁ ተሳትፎ በስራቸው 22 ሴቶችን ይመራሉ፡፡ እሳቸው ከፕሮጀክቱ የሰለጠኑትን እውቀት በወር ሁለት ጊዜ ለቡድናቸው እያሰለጠኑ ሁሉም በስሥነ-ፅዳት ሞዴል እንዲሆኑ ጥረት አድርገዋል፡፡ የወንዶች እና የሴቶች ብለው ለይተው መፀዳጃ ቤት ሰርተዋል፡፡ በዚህም በአካባቢያቸው የሰው እዳሪ እንደሌለ ተናግረዋል፡፡ ቤተሰቡ የሚታጠብበትን ሻወር ቤት የወንድ እና የሴት ብለው ከፍለው ሰርተዋል፡፡ ሁሉም የቤተሰቡ አባላት በወሳኝ የእጅ መታጠቢያ ጊዜያት ማለትም ጥዋት፣ ከምግብ በፊት፣ ከምግብ በኋላ እና ከሽንት ቤት መልስ እጃቸውን ይታጠባሉ፡፡ አሁን ቤተሰቡ ጤናማ ሁኗል፡፡ "እኔ ግንባር ቀደም ሁኜ እሰራለሁ፡፡ የወንድ እና የሴት መፀዳጃ ቤት እና ሻወር ቤት አለኝ፡፡ የውሃ ማጣሪያ ቱሊፕ ገዝቻለሁ፡፡ አሁን ቤተሰቤ ሙሉ ጤነኛ ነው፡፡ አካባቢያችንም ንፁህ ማዕዛ ሞልቶታል" ሲሉ / ማስተዋል ተናግረዋል::

/ አባይ ሰውነት የቀበሌው የጤና ኤክሰቴንሽን ባለሙያ ናቸው፡፡ ባላሙያዋ እንዳሉት ፕሮጀክቱ በሰራው ስራ የቀበሌው ነዋሪዎች ልሾ ወይም ስላቭ ያለው መፀዳጃ ቤት፣ የተሻሻለ ሻወር ቤት እና ጭሽ አልባ ምድጃ ገንብተው እየተጠቀሙ ነው፡፡

በአመልድ ኢትዮጵያ ጆን ሪግ ዋሽ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ አደራጅ ሙሉቀን እንዳሉት ፕሮጀክቱ በሚተገበርባቸው ወረዳዎች የማህበረሰቡን የአካባቢ ንጽህና እና የግል ንፅና ለመጠበቅ 2009 . እስከ 2013 . 79 የውሃ ተቋማትን (5 ጥልቅ ጉድጓዶች 71 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ እና 3 ትልልቅ ምንጭ ማጎልበት) ገንብቶ 68ሺህ የሚጠጉ ተጠቃሚዎችን የንፁህ መጠጥ ውሃ ተደራሽ አድርጓል፡፡ በዚህም የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋንን ማሻሻል ተችሏል፡፡ በተለይም የፕሮጀክቱ ተጠቃሚዎችን የአካባቢ ንፅህና ለመጠበቅ ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ አባላት እና ለክሊኒኮች የሚያገለግሉ 25 ብሎክ ዘመናዊ መፀዳጃ ቤቶችን ገንብቶ አስረክቧል፡፡ በተጨማሪም አርሶ አደሮች አገልግሎት በሚያገኙባቸው የቀበሌ ማዕከላት 56 ሞዴል መፀዳጃ ቤቶች ገንብቶ በማስረከብ በሜዳ መፀዳዳት እንዲቀር ጉልህ ሚና ተጫውቷል ብለዋል፡፡ በአጠቃላይ ገዳማዊት ቀበሌ ላይ በተሰራው ሞዴል የሆነ የስነ-ንፅህና ስራ ሌሎች ወረዳዎች እና ዞኖች እየመጡ ተሞክሮውን በመውሰድ ላይ ናቸው ብለዋል፡፡ በቀጣይም መልካም ተሞክሮውን ለማስፋት ይሰራል ተብሏል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today60
Week154
All83648

Currently are 19 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?