Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች በቁጥቋጦ የተሸፈኑ ተፋሰሶችን በፍራፍሬ ማልማት

     በቁጥቋጦ የተሸፈኑ ተፋሰሶችን በፍራፍሬ ማልማት

      Covering a bush land with a fruit (1)

በኢትዮጵያ ሰፊ ተራራማ መሬት ተራቁቶ እና በቁጥቋጦ ተሸፍኖ ይገኛል፡፡ ይህንን የመሬት ሃብት እንዲያገግም ማድረግ እና ጥቅም በሚሰጡ ፍራፍሬዎች በመተካት የአካባቢው አርሶ አደሮች ገቢያቸው እንዲሻሻል ያግዛል፡፡ በመሆኑም በአመልድ ኢትዮጵያ ግሮውዝ 4 ዘፊውቸር፡ የተጠናከረ፣ቀልጣፋና ቀጣይነት ያለው የግብይት ስርዓት ለዘላቂ ኑሮ መሻሻል ፕሮጀክት በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን አምባሰል እና ተሁለደሬ ወረዳዎች እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን ደዋ ጨፋ ወረዳ .. ሐምሌ 2020 ጀምሮ በተራቆቱ ተፋሰሶች ላይ የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም በመስራት፣ አትክልት እና ፍራፍሬ በማልማት የአርሶ አደሩን ገቢ ለማሻሻል ይሰራል፡፡

ፕሮጀክቱ ከሲውድን አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ደርጅት ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ በፋርም አፍሪካ፣ አመልድ ኢትዮጵያ እና ሜርሲ ኮርፕስ ትብብር ይተገበራል፡፡ የተሻለ የገበያ ስርዓት በመዘርጋት 10ሺህ አርሶ አደሮችን ገቢ በማሻሻል የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው፡፡ የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት በማሳደግ የኑሮ መሻሻል ለማምጣት የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ስራዎች በተጎዱ ተፋሰሶች እየተሰሩ ነው፡፡ በዚህም በተለያዩ ተፋሰሶች 33 ሄክታር ላይ የተቀናጀ የመሬት አጠቃቀም ስራ ተሰርቷል፡፡ በተለይም በቁጥቋጦ ተሸፍነው ጥቅም ላይ ያልዋሉ ተራራማ ተፋሰሶችን የጠረጼዛ እርከን በመስራት 52 የተደራጁ ወጣቶች አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲያለሙባቸው ሁኗል፡፡ ለአብነትም በአምባሰል ወረዳ ሮቢት ቀበሌ ድሃዲት ተፋሰስ እና በደዋ ጨፋ ወረዳ ሲትር ቀበሌ ሃሮየ ተፋሰስ ላይ የተሰሩ ስራዎች ምስክር ናቸው፡፡

       Covering a bush land with a fruit (2)1

በሃሮየ ተፋሰስ 35 ወጣቶች በማህበር ተደራጅተው 600 በላይ የማንጎ ችግኞችን 12 ሄክታር ማሳ ላይ በሚያዚያ 2013 . ተክለዋል፡፡ ከማህበሩ አባለት መካል ወጣት አቫድር አንዱ ነው፡፡ "ከዚህ በፊት ስራ አልነበረንም፤ አሁን በዚህ ተፋሰስ ላይ የስራ ዕድል ተፈጥሮልናል፤ ማንጎ ተክለናል፡፡ በቀጣይ የቦቆሎ ዘር እና የበርበሬ ዘር መጥቶልናል በጥምር ግብርና ለመዝራት እያዘጋጀን ነው፤ ተስፋችን እና መዳረሻችን ትልቅ ነው" ሲል ወጣት አቫድር ተናግሯል፡፡ እንዲሁም በአምባሰል ወረዳ፣ ሮቢት ቀበሌ በድሃዲት ተፋሰስ ተጠቃሚ ከሆኑ ወጣቶች መካከል 17 አባላት ያሉት ማህበር አባል የሆነው ሽመልስ አያሌው አንዱ ነው፡፡ ወጣት ሽመልስ እንዳለው በተፋሰሱ ፓፓያ፣ አቮካዶ፣ ማንጎ እና ቦቆሎ በስብጥር እያለሙ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ ጓንጉል ተገኘ "የተፋሰስ ልማቱ የአካባቢዎችን ወጣቶች በግብራና ስራ ተሰማርተው የስራ እድል እንዲፈጥሩ እና የገቢ አማራጫቸውን እንዲያሰፉ ትልቅ ሚና ይጫወታል" ብለዋል፡፡ "ቋሚ የፍራፍሬ ተክሎችን ማለትም ማንጎ እና አቮካዶ ችግኞችን በማቅረብ እንዲተክሉ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም በጥምር ግብርና ለማልማት የቲማቲም፣ ቃርያ፣ ፓፓያ እና የቦቆሎ ዘሮችን በማቅረብ ተፋሰሱን በሰብል ለመሸፈን ሰፊ ስራ ተሰርቷል፡፡ ፍራፍሬዎች በበጋ እንዳይደርቁ ትልልቅ የውሃ ሮቶዎች እና የውሃ ማስተላለፊያ ቱቦዎች ዝርጋታ ተከናውኗል" ብለዋል፡፡ ስለዚህ ወጣቶች ተፋሰሳቸውን በአግባቡ በመንከባከብ የግብርና ስራቸውን በትጋት እና በቁርጠኝነት መስራት ይገባቸዋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today60
Week154
All83648

Currently are 20 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?