Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች የጌደብ የመስኖ ልማት

                 የጌደብ የመስኖ ልማት

        Gedeb Irrigation 1

አርሶ አደሩ ከዝናብ ጥገኝነት ተላቆ ምርታማ እንዲሆን የመስኖ ልማት ስራዎቻችን ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ የደን ልማት ስራዎችን በማጠናከር፣ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ፣ የንጹህ መጠጥ ውሃ በማድረስ፣ የግልና የአካባቢ ንጽህናን በመጠበቅና ትራኮማን በመከላከል፣ አነስተኛ የመስኖ አውታሮችን በመዘርጋት፣ ስርዓተ-ምግብን በማሻሻልና መቀንጨርን በመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

        Gedeb Irrigation

አርሶ አደር አያሌው ፈረደ በምስራቅ ጎጃም ዞን የማቻክል ወረዳ ግሩም የሳንቃት ቀበሌ ኗሪ ናቸው፡፡ አመልድ የጌደብን ወንዝ ጠልፎ ዘመናዊ የመስኖ ልማት በመገንባቱ አርሶ አደሮች ተጠቃሚ መሆን እንደቻሉ ይናገራሉ፡፡ ገና በመስኖ መጠቀም የጀመሩት 2005 . ሲሆን 2006 . ሩብ ሄክታር በማትሞላው ማሳቸው 30 ኩንታል ድንች አምርተው 6 ሺህ ብር በላይ በመሸጥ ሰባ አምስት ዚንጎ ቆርቆሮ ቤት ሰርተዋል፡፡ የመስኖ ልማት በመጠቀማቸው በኑሯቸው እየተለወጡ እንደሚገኙ የሚገልጹት አርሶ አደሩ በማሳቸው የሚያልፈውን ውሃ በመጠቀም ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩ፣ ሃብት እንዲያፈሩ አድርጓቸዋል፡፡

የክልላችን ብሎም የሃገራችን አርሶ አደሮች አነስተኛ ማሳ ይዞታ ያላቸው በመሆኑ በአነስተኛ ማሳቸው ከሁለት ጊዜ በላይ እንዲያመርቱ፣ በትንሽ ማሳ ብዙ ምርት እንዲያገኙና ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል አነስተኛ የመስኖ ልማቶች አነስተኛ ማሳ ላላቸው አርሶ አደሮች እጅግ ወሳኝ ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ በመስኖ ሊለማ የሚችል 5.3 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡ ነገር ግን ሃገሪቱ ካላት እምቅ የመስኖ አቅም ሁለት ሚሊዮን ወይንም 38 በመቶ ብቻ እየለማ እንዳለ ነው የግብርና ሚኒስቴር መረጃ የሚያሳየው፡፡ በመስኖ የማልማት አቅማችንን ለማሳደግም በክልላችን መጠነ-ሰፊ የመስኖ ልማት አውታሮች እየተዘረጉ ይገኛሉ፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ ጥራቱ ጥራቱን የጠበቀ ውጤታማ የመስኖ ግንባታዎችን በማከናወን ረገድ ግንባር ቀደም መሆን ችሏል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today46
Week201
All74899

Currently are 21 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?