Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች አመልድ ኢትዮጵያ በ12.5 ሚሊዮን ብር የገነባው የሳጋ መስኖ ልማት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ 12.5 ሚሊዮን ብር የገነባው የሳጋ መስኖ ልማት አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ ነው፡፡

       Saga small scale irrigation

አመልድ ኢትዮጵያ በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ 12.5 ሚሊዮን ብር የገነባው የሳጋ መስኖ ልማት 393 አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ እያደረገ እንደሚገኝ የድርጅቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ደጀኔ ምንልኩ ተናገሩ፡፡

2012 . ተጀምሮ በአንድ ዓመት የተጠናቀቀው ይህ የመስኖ ልማት 95 ሄክታር መሬት የሚያለማና የአካባቢውን አርሶ አደሮች ኑሮ እየለወጠ መሆኑን የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ ገልጸዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው አክለውም ኘሮጀክቱን በጥራትና በአጭር ጊዜ ውጤታማ ያደረገውን አመልድ ኢትዮጵያን አመስግነው የአካባቢው ህብረተሰብና የወረዳ አመራሩ የነበራቸው ድጋፍና ሃላፊነትም ከፍተኛ መሆኑን አውስተዋል፡፡

በርክክቡ ወቅት የተገኙት የኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሚኒስቴር / ሂሩት ካሳው አመልድ ለምነታቸውን ያጡ መሬትን በማልማትና በደን በመሸፈን በክልሉ እየሰራ የሚገኝ ዕውቅና የምሰጠው ድርጅት ነው ብለዋል፡፡

በአመልድ ኢትዮጵያ ፈጻሚነት የሚተገበረው ሁለተኛው /ዘላቂ የምግብና ስርዓተ-ምግብ ዋስትና ልማት ፕሮጀክት- Sustainable Food and Nutrition Security /SFNS/ Project በጀርመን የኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴርና /BMZ/ ልት ሁንገር ሂልፈ እና ከክልሉ መንግስት በተገኘ 55 ሚሊዮን ብር በእስቴ፣ ጉና በጌ ምድር፣ ፎገራና ፋርጣ ወረዳዎች 13,284 ተጠቃሚዎችን ህይወት ለመቀየር የተለያዩ የኑሮ ማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡      

ፕሮጀክቱ የአርሶ አደሩን ምርታማነት ለማሳደግ የተሻሻሉ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን እንደ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ባቄላ፣ ድንች፣ ሽንኩርት፣ጥቅል ጎመን፣ እንቁላል ጣይ ዶሮ፣ የዋሸራ በግ ወዘተ ላይ በማሳተፍ በቤተሰብ ደረጃ በተለይ 2 ዓመት ያልሞላቸው ህጻናት፣ አጥቢና ነፍሰ-ጡር እናቶች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ አድርጓል፤ ለገበያ በማቅረብም የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል፡፡

        Saga small scale irrigation 3

ተጠቃሚዎች በመንደር ብድርና ቁጠባ እንዲቆጥቡና በተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያዩም ይደረጋል፤ ስርዓተ-ጾታ፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ህጻናት አመጋገብና ግጭት አፈታት ዙሪያ ስልጠና ወስደው ኑሯቸውን ለማሻሻል በተግባር ልምምድ እያደረጉ ናቸው፡፡ ለአብነት ወንዶች የሴቶችን የስራ ጫና በመረዳት እንጀራ መጋገር፣ ቡና ማፍላት፣ ህጻናትን መመገብባ መንከባከብ ጀምረዋል፡፡

        Saga small scale irrigation 1

በእስቴ ወረዳ የደንጎልት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት 28 ዓመቱ ወጣት አርሶ አደር ኮከብ ምሬ ባለትዳርና 1 ልጅ አባት ናቸው፡፡ አርሶ አደሩ መስኖው ከመገንባቱ በፊት አነስተኛ ማሳው ላይ በቂ ምርት ስለማያገኝ ለጉልበት ስራ ወደ ሌላ ቦታ ይሰደድ እንደነበር ይናገራል፡፡ ሆኖም የሳጋ መስኖ በመጠናቀቁ 2013 . በመስኖንች ምርት 102 ኩንታል በላይ የድንች ምርት አምርቶ 75 ሺህ ብር በላይ ማግኘት ችሏል፡፡ በቀጣይም ቲማቲም፣ ቃሪያ፣ ጎመን እና ሃብ ሃብ ለማምረት መሬቱን እያዘጋጀ እንደሆነ ያስረዳል፡፡

       Saga small scale irrigation (1)

አርሶ አደር አየነው ብርሃን በእስቴ ወረዳ የሽማግሌ ጊዮርጊስ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው፡፡ የዋሸራ በግ አውራ በማግኘታቸው በአጠቃላይ 40 የተዳቀሉ በጎችን አርብተው 60 ሺህ ብር በላይ አግኝተዋል፡፡ ፕሮጀክቱ በኩታ ገጠም ማሳ የተሻሻለና በሽታ የሚቋቋም ስንዴ በማቅረቡም የተሻለ ምርት ማግኘታቸውንና በኑሯው መለወጣቸውን ይናገራሉ፡፡

በተጨማሪም አመልድ ኢትዮጵያ 2008 . የመተረይን መስኖ ገንብቶ በማስረከቡ እና የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ስላቀረበልን ከቤት ፍጆታ ባሻገር ለገበያ ማቅረብ ችለናል፡፡ በኑራችንም ደስተኞች ነን፡፡ በወንዙ ምክንያት በሞቱ ወገኖቻችን ብናዝንም ዛሬ ግን በመገደቡ ምክንያት በመስኖው እየተጠቀምን ነው፡፡" ይላሉ በምስራቅ እስቴ ወረዳ የመተረይ መስኖ ተጠቃሚ አርሶአደሮች፡፡

በአጠቃላይፕሮጀክቱ፡-

የተሻሻሉ የሰብልና እንስሳት ዝርያ አቅርቦት

የመስኖ አውታር ግንባታ

የመንደር ብድርና ቁጠባ

የስራ ዕድል ፈጠራና የገበያ ትስስር

የስርዓተ-ጾታና ህጻናት አመጋገብ

የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት

የወጣቶች ስራ ዕድል (በተለይ በማድለብና ሌሎች ስራ መስኮች) ተጠቃሚዎች የተሻለ ኑሮ እንዲኖራቸው ማስቻል ዋና ዋና ተግባራቶቹ ናቸው፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ አጋሮቻችን #የጀርመን ህዝብ እና መንግስት በተጠቃሚዎች ስም እናመሰግናለን::

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today42
Week434
All80029

Currently are 27 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?