Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች የቧሽከረና የመስኖ ልማት ፍሬ አፍርቷል

        የቧሽከረና የመስኖ ልማት ፍሬ አፍርቷል

       Buashkerna Irrigation

በዳህና ወረዳ ወረዳ ቀበሌ 15 ምራው ጎጥ ወስጥ የቧሽከረና መስኖ ልማት በአመልድ ኢትዮጵያ አራተኛው ልማታዊ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም 4 ተቋማትንና አይበገሬነትን ማጠናከር ፕሮጀክት 4 ዓመት በፊት ነበር የተገነባው፡፡ የመስኖ ልማቱ ከተገነባ በኋላ አርሶ አደሮች የተለያዩ ቋሚ አትክልቶችን በወቅቱ ሲተክሉ ነበር፡፡ ከተጠቃሚ አርሶ አደሮች አንዱ 45 ዓመቱ ጎልማሳ እምወደው መንግስቴ አንዱ ነው፡፡

አርሶ አደር እምወደው የመስኖ ልማቱ 4ዓመት በፊት ሲገነባ በሸለቆ ውስጥ የምትገኘውን ማሳውን በቋሚ አትክልት ለማልማት ተነሳሳ፡፡ በወቅቱም ዘይቶን፣ ሸንኮራ አገዳ እና ሌሎች ቅመማ ቅመሞችን አልማቷል፡፡ አሁን የማሳውን ፍሬ መቅመስ ጀምሯል፡፡ "ከዚህ በፊት 2 ጥማድ መሬት ነበረኝ፣ በአመት አንድ ጊዜ ነው የማመርተው፡፡ ሁሉንም ወጪ የምሸፈነው ከዚህ ገቢ ነበር፡፡ በቀላሉ የቤት ወጪ እና ለልጆች /ቤት ወጪ ማግኘት ከባድ ነበር" ይላል፡፡

        Buashkerna Irrigation1

አርሶ አደር እምወደው አሁን ከሸንኮራ እና ዘይቶን ምርት ብቻ ባለፉት 2 ዓመታት 19 ሺህ ብር በላይ አግኝቷል፡፡ በዚህም አስቸጋሪ ኑሮውን አቃሎለታል፡፡ "ከመስኖ ልማቱ ገቢ በማግኘቴ የምግብ እህል አልሸጥሁም፣ እንደውም ከመስኖው ባገኘሁት ገቢ ቆርቆሮ ቤት ሰርቻለሁ፣ እንዲሁም የግብርና ስራየን ለማሻሻል በሬ፣ላም እና አህያ ገዝቼ እየተጠቀምሁ ነው" ብሏል፡፡ በተመሳሳይ ሌሎች የአካባቢው አርሶ አደሮችም በመስኖ ልማቱ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት በመጀመራቸው ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ገልፀውልናል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today48
Week203
All74901

Currently are 25 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?