Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ዜና የቅርብ ዜናዎች “አመልድ ኢትዮጵያ ከጎሰቆለ ኑሮ አውጥቶናል”

      “አመልድ ኢትዮጵያ ከጎሰቆለ ኑሮ አውጥቶናል

        miserable life

ወጣት አርሶ አደር አበበ መኮንን በቂ የእርሻ መሬት ባለመኖሩ ቤተሰቡን ለማስተዳደር የቀን ስራ በመስራት ገንዘብ ለማግኘት ይታተር ነበር፡፡ ነገር ግን የቤተሰቡን የምግብ ወጪ እና ሌሎች ማህበራዊ ወጪዎችን ለመሸፈን ይቸገር ነበር፡፡ ወጣት አበባው በሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ 03 ሃሙሲት ቀበሌ ነዋሪ 32 ዓመት ወጣት ሲሆን ባለትዳር እና 3 ልጆች አባት ነው፡፡

4 ዓመት በፊት በአመልድ ኢትዮጵያ አራተኛው ልማታዊ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም 4 ተቋማትንና አይበገሬነትን ማጠናከር ፕሮጀክት (DFSA) ከአሜሪካ ህዝብና መንግስት በተገኘ $ 86.6 ሚሊዮን የገንዘብ ድጋፍ ከኬር ኢትዮጵያ እና ወርልድ ቪዥን ጋር በመተባበር በአማራ ክልል 9 ወረዳዎች፡ ቡግና፣ መቄት፣ ላስታ፣ዋድላ፣ ጋዞ፣ ዳህና፣ ሰቆጣ፣ፃግብጅ እና ጋዝጊብላ ወረዳዎች ለምግብ ዋስትና ተጋላጭ የሆኑ ነዋሪዎችን ኑሮ ለማሻሻል መተግበር የጀመረበት ጊዜ ነበር፡፡ ፕሮጀክቱ ሲጀምር እርሱም በፕሮጀክቱ ታቅፎ ኑሮውን ለማሻሻል ዕድል አገኘ፡፡

       miserable life1

ፕሮጀክቱ በሰቆጣ ዙሪያ ወረዳ 03 ሃሙሲት ቀበሌ 124 ቤተሰቦችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የሻልጣኑ መስኖ ግንባታ 3 ዓመት በፊት ገንብቷል፡፡ ወጣት አርሶ አደር አበበ መኮንን አንዱ ተጠቃሚ ነው፡፡ ባለችው አነስተኛ ማሳ ጥቅል ጎመን፣ካሮት፣ቆስጣ፣ሸንኮራ አገዳ፣ ፓፓያ እና ቡና ማልማት ጀመረ፡፡ በዚህም ባለፉት 3 ዓመታት ካለማው ምርት 25ሺህ ብር ገቢ አግኝቷል፡፡ "አመልድ ኢትዮጵያ ከጉስቁልና አውጥቶናል፤ ቀለብ የሸመትሁት፣ ለልጆቼ ልብስ የገዛሁት ከመስኖ ልማት ገቢ ነው፡፡ የአመልድ ኢትዮጵያ ባንዲራው ሁሌም ከፍ ይበል" ብሏል፡፡

በአመልድ ኢትዮጵያ አራተኛው ልማታዊ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም 4 ተቋማትንና አይበገሬነትን ማጠናከር ሰቆጣ ፕሮጀክት ማናጀር አቶ ቤተስላሴ እንዳሉት የመስኖ ልማቱ የአካባቢውን አርሶ አደሮች ከስደት ህይዎት የታደገ ነው፡፡ የዚህን መልካም ተሞክሮ ለማስፋት የሸንኮርትኩ የመስኖ ልማት ግንባታ በወረዳው እየተካሄደ ነው ብለዋል፡፡

 


Language Selection
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ
የጎብኝዎች ብዛት
Today48
Week203
All74901

Currently are 15 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?