Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ ዜና

ዜና

   በአቅራቢያቸው የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሆኑት እናት!

     A Clean Water Beneficiary Woman (1)

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ከቻሪቲ ወተር በተገኘ 68.8 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ ላለፉት ሁለት ዓመታት (2011 . እና 2012 .) በሰሜን ሸዋ ዞን ሲያደብርና ዋዩ፣ ባሶና ወራና እንዲሁም አንጎለላና ጠራ ወረዳዎች 172 የንጹህ መጠጥ ውሃ ተቋማትን በማጎልበት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

/ ጽጌ ሽፈራው 48 ዓመት አዛውንት ሲሆኑ ባለትዳርና 7 ልጆች (ወንድ 4 ሴት 3) እናት ናቸው፡፡ በአንጎለላና ጠራ ወረዳ ጨፋናን ቀበሌ ግንደበር ጎጥ ነዋሪ የሆኑት / ጽጌ ለረጅም ዓመታት በውሃ ችግር ምክንያት ሲንገላቱ ኖረዋል፡፡
ቀደም ሲል ጨፌ ከሚባል ምንጭ እና ከጫጫ ወንዝ ነበር ውሃ የሚያገኙት፡፡ ይሁን እንጅ ከምንጯ የሚገኘው ውሃ በቂ ባለመሆኑ የአካባቢው ነዋሪዎች በጨለማ ሌሊት ተጉዘው በወረፋ ነበር የሚቀዱት፡፡ አመልድ ለነዋሪው ገንብቶት የነበረው የምንጭ ማጎልበት ላለፉት 14 ዓመታት በሚገባ ሲያገለግል ቆይቶ ዛሬ ላይ ሙሉ በሙሉ ደርቆ አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡

ምንጯ ስትቀንስባቸው ደግሞ ውሃ የሚቀዱት የወረዳው መናገሻ ከተማ ከሆነችው ጫጫ በመሄድ ከግለሰቦች እንደነበርና ውሃ ቀድቶ ለመመለስ አንድ ሰዓት ይወስድ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ቤተሰቡ ህጻናትን ጨምሮ ምግብ በሰዓቱ አዘጋጅተው መመገብ ሳይችሉ ቆይተዋል፡፡ የግልና የአካባቢ ንጽህናም ሲጓደል ቆይቷል፡፡

በአካባቢው የአልፋ ንጹህ መጠጥ ውሃ ማምረቻ ድርጅት መኖሩ ለአካባቢው ህብረተሰብ የንጹህ መጠጥ ውሃ እንዲያገኙ አመቻችቷል፡፡ ይሁን እንጅ ህብረተሰቡ አንድ ሰዓት መጓዝ የሚጠይቅ ከመሆኑም ባሻገር አውራ መንገድ ማቋረጥ ግድ ስለሚል ለተለያዩ የትራፊክ አደጋዎች እየተጋለጡ ቆይተዋል፡፡

      A Clean Water Beneficiary Woman (2)

በአሁኑ ሰዓት አመልድ በአቅራቢያቸው የንጹህ መጠጥ ውሃ ገንብቶ አስረክቧቸዋል፡፡ ድርጅቱ የአካባቢው ማኅበረሰብ ኑሮው እንዲሻሻል ያበረከተው አስተዋጽኦ በእጅጉ ከፍተኛ ነው፡፡ በተለይ የሴቶችንና ህጻናን ችግር መቅረፍ ችሏል፡፡

/ ጽጌ "ካሁን ቀደም የቆየውን ችግራችን አመልድ ከቻሪቲ ወተር ጋር በመተባበር በአቅራቢያችን ንጹህ ውሃ እንድንጠቀም ረድቶናል፡፡ እኛም ልጆቻችንም ከውሃ ወለድ በሽታ ተገላግለናል፡፡ ጊዜያችንንና ጉልበታችንን ቆጥቦልናል፡፡ ተማሪ ልጆቻችንም የትምህርት ሰዓታቸውን አያባክኑም፡፡ የምንፈልገውን በቂ ውሃም አግኝተናል፤በጣም ደስ ብሎናል፡፡" ሲሉ ይገልጻሉ፡፡

የአካባቢው ህብረተሰብ በምንጭ ማጎልበት ስራው ተሳትፎ አድርጓል፡፡ የድንጋይ፣ የአካባቢ ቁሳቁስ እና የጉልበት ድጋፍም አድርገዋል፡፡

 

"ከምንጠጣው ኩሬ ውስጥ በተገኘው ነገር ተደናግጠን ሩቅ ወንዝ እየሄድን እንቀዳ ነበር"- አርሶ አደር አለልኝ ጌታሁን

      farmer Alelign Getahun. (2)

በአመልድ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት ከግሊመር ኦፍ ሆፕ ግብረ-ሰናይ ድርጅት በተገኘ 83 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በሊቦከምከም ወረዳ 9 ቀበሌዎች .. 2018 ጀምሮ በንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ በሬ በማድለብ፣በግ በማርባት እና ማድለብ፣ ፍየል እና ዶሮ በማርባት እና ሽንኩርት በማልማት 1 ሺህ 79 አርሶ አደሮች በፕሮጀክቱ ታቅፈው ኑሯቸውን ለማሻሻል እየሰሩ ነው፡፡

በፕሮጀክቱ የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ከሆኑት መካከል የአንጎት ቀበሌ ነዋሪው አርሶ አደር አለልኝ ጌታሁን አንዱ ናቸው፡፡ አርሶ አደር አለልኝ 38 ዓመት ጎልማሳ እና የሦስት ልጆች (ሴ፡1) አባት ናቸው፡፡ ኑሯቸውን በግብርና ስራ እየመሩ የሞቀ ቤተሰብ መስርተዋል፡፡ ነገር ግን በአካባቢያቸው ንፁህ የመጠጥ ውሃ እጥረት ጋር በተያያዘ በሚያጋጥሙ የጤና ችግሮች ምክንያት የቤተሰባቸው ሰላም የሚናጋበት ወቅት ነበር፡፡

በአመልድ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታ ከማግኘታቸው በፊት በአንድ ወቅት የእርሳቸውን ቤተሰብ ጨምሮ ለአካባቢው ህዝብ ያስጨነቀ ጉዳይ አጋጥሟቸው ነበር፡፡ በአካባቢው አንድ ውሻ ከታመመ በኋላ አድራሻው ይጠፋል፡፡ ባለቤቶቹም በውሻቸው መጥፋት ተስፋ ቆርጠው በተቀመጡበት ጊዜ አንድ መጥፎ ዜና ለመንደሯ ነዋዎች ደረሳቸው፡፡ ያም ከሚጠጡት ምንጭ አናት ላይ ካለ ኩሬ የሞተ ውሻ ሽታ እንዳለ የሚያሳይ መረጃ ነበር፡፡ በወቅቱም የተሰማቸውን ስሜት አርሶ አደር አለልኝ ሲያስታውሱ "ባለቤቴ ውሃ ምትቀዳው አጫ ከሚባል ኩሬ ነበር፡፡ አንድ ጊዜ ከኩሬው ውሻ ገብቶ ሳናየው ሰጥሞ ሙቶ ተገኘ፡፡ የሞተውን ውሻ ከኩሬው ያወጣሁት እኔ ነበርሁ፡፡ በአካባቢው ከዚህ ኩሬ 16 አባውራዎች ተጠቃሚ ነበሩ፡፡ ሁላችንም ባገኘነው ነገር ተደናግጠን ከሩቅ ወንዝ ለአንድ ሰዓት እየሄድን ውሃ እንቀዳ ነበር፡፡ በኋላ ውሻው በእብድ ውሻ በሽታ ነው የሞተ ተብሎ ሁሉም ተጠቃሚ ባህላዊ መድሃኒት ፍለጋ /ታቦር ከተማ እየሄድን ስንታከም ነበር፡፡ እኔ በግሌ 1ሺህ 600 ብር በላይ ወጪ አውጥቻለሁ፡፡ የነበረብን ማህበራዊ ጭንቀት ቀላል አልነበረም" ብሏል፡፡

      farmer Alelign Getahun. (1)

አሁን በአመልድ የተቀናጀ የማህበረሰብ ልማት ፕሮጀክት የንፁህ መጠጥ ውሃ ተገንብቶላቸው ደስታቸው የላቀ ሁኗል፡፡ "አሁን ንፅህናው የተጠበቀ ጣፋጭ ውሃ በቀላሉ አግኝተናል፡፡ የባለቤቴ እና የልጆቼ ድካም ተቀርፏል፡፡ እኛም ደስ በሎን ውሃ እየጠጣን ነው፡፡ አመልድ እና የግሊመር ኦፍ ሆፕ ድርጅት የህዝብን ህይዎት እየታደጉ ነው" ብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ በወረዳው 17 ሺህ 176 ነዋሪዎችን (ሴ፡ 8,457) ተጠቃሚ ያደረጉ 50 የውሃ ተቋማት ማለትም 26 ጥልቅ ውሃ ጉድጓዶች፣17 የእጅ ውሃ ጉድጓድ እና 7 የምንጭ ማጎልበት ግንባታዎች ተሰርተዋል፡፡

የውሃ ተቋሙ ሳይበላሽ ለብዙ ዓመታት አገልግሎት እንዲሰጥ የተጠቃሚዎች ኮሚቴ ክትትል ያደርጋል፣ዘበኛ መድቦ ያስጠብቃል፡፡ የውሃ ግንባታው ቢበላሽ ለማስጠገን እያንዳንዱ ተጠቃሚ በወር አምስት ብር እየቆጠ ይገኛል፡፡ ውሃውን የሚንከባከቡ፣ ቢበላሽ የሚጠግኑ ራሳቸው የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡

Read more...

 
More Articles...


ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today0
Week300
All64230

Currently are 8 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?