Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ስለ አመልድ ኢትዮጵያ የአመልድ ኢትዮጵያ ፕሮፋይል

mGb!Ã

አመልድ ኢትዮጵያ በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ድርቅና የእርስ በርስ  ጦርነት ይሰቃይ የነበረውን ህዝብ ለመርዳት በጎ ፈቃደኞች አማካይነት የካቲት 1976 ዓ.ም ተቋቋመ፡፡  በወቅቱ የኢትዮጵያ ዕርዳታ ማስተባበሪያ ድርጅት (ኢዕማድ) የሚል ስያሜ የነበረው ሲሆን እስከ 1983 . ድረስ ባሉት ጊዜያት በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ ከስቃይ፣ ከስደትና ከሞት አደጋ ለመታደግ የቻለ ጠንካራ ድርጅት ነው፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 ዓ.ም አንቀጽ 68 መሰረት በመዝገብ ቁጥር 0607 ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገ መንግስታዊ ያልሆነ እና ለትርፍ ያልተቋቋመ አገር በቀል የልማት ድርጅት ነው፡፡

እ.ኤ.አ በ1991 የደርግ ውድቀት በኋላ የውስጥ ሁኔታው የተረጋጋ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እንዲሰሩ የሚያስችላቸው ነበር፡፡ በመሆኑም ኢሮ (ERO) ከሱዳን የተመለሱ ኢትዮጵያውያንን ወደ አገራቸው መመለስ እና በሀገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎችን ማስፈርን ጨምሮ የእርዳታ እና የግብርና ስራን ድጋፍ ማድረግ ላይ አተኮረ፡፡ እ.ኤ.አ ከ1993 ጀምሮ የልማት ስራዎች ላይ በመሰማራት በእብናት ፣ በለሳ ፣ በሰቆጣ እና በመተማ ወረዳዎች የተቀናጀ የምግብ ዋስትና እና የገጠር ልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ አደረገ፡፡ ሆኖም እስከ 1997 ድረስ በስትራቴጂክ ዕቅድ አልተመራም፡፡ አመልድ ኢትዮጵያ ሚያዝያ 1997 በባህር ዳር በተካሄደው ሁለተኛው ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት የመጀመሪያውን የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ (1997 - 2003) ያከናወነ ሲሆን በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ወቅት ነው ስሙ ከኢሮ ወደ የአማራ መልሶ መቋቋም ልማት ድርጅተ (አመልድ) የተቀየረው፡፡ በመቀጠልም በ6ኛው ስትራቴጅክ እቅዱ በመላ ኢትዮጵያ ስራዎችን ለመስራት ባስቀመጠው እቅድ መሰረት የአማራ መልሶ መቋቋም ልማት ድርጅተ (አመልድ) የሚለው ስሙ ወደ አመልድ ኢትዮጵያ ተቀይሯል፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ መጀመሪያው የስትራቴጂክ እቅድ በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ፣ በግብርና ልማት ፣ በገጠር ንፁህ ውሃ አቅርቦት እና በመንገድ ግንባታ ላይ እንዲያተኩር ቅድሚያ ይሰጥ ነበር፡፡ አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እና ሌሎች ተያያዥ ድጋፎች አስፈላጊ በሚሆኑበት ጊዜ ብቻ ይሰሩ ነበር፡፡ በዚህ ወቅት ድርጅቱ በሰቆጣ ፣ በእብናት ፣ በለሳ ፣ በዋድላ ፣ ታች ጋይንት ፣ ላይ ጋይንት ፣ ጉባላፍቶ እና ግዳን ወረዳዎች ውስጥ 7 የምግብ ዋስትና እና የተቀናጀ የገጠር ልማት ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ አድርጓል፡፡

ሁለተኛው የስትራቴጂክ ዕቅድ (እ.ኤ.አ. 2004 - 2008) ቀደም ሲል ቅድሚያ ትኩረት የተሰጣቸውን ጉዳዮች አጣርቶ በአምስት ፕሮግራሞች ማለትም በግብርና ልማትና አካባቢ ጥበቃ ፣ በደን ሃብት ልማት ፣ በውሀ ሀብት ልማት ፣ በአቅም ግንባታ እና በማህበረሰብ ልማት እና በአደጋ መከላከል እና እርዳታ ፕሮግራሞች ፣ ከስድስት ደጋፊ ክፍሎች ጋር ተተግብሯል። ይህ የስትራቴጂክ ዘመን አመልድ ኢትዮጵያ በሕዝብ ፣ በመንግስት ፣ በለጋሾች እና በአጋሮች መካከል በከፍተኛ ደረጃ እውቅና ያገኘበት እና ትልቅ አሻራ ያስቀመጠበት ነበር፡፡

በሶስተኛው የስትራቴጂክ እቅዱ /ከ2000 ዓ.ም እስከ 2005 ዓ.ም/ በዕለት ዕርዳታና በመልሶ መቋቋም፣  በተፈጥሮ ሀብት፣ በንጹህ መጠጥ ውሃና መስኖ ልማት እንዲሁም በግብርና ልማት፣ በተቋማዊ ቅም ግንባታና ሁለገብ ተግባራትን በመፈጸም ሚሊዮኖችን ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

በ4ኛው የስትራቴጅክ እቅድ /ከ2006 እስከ 2010 ዓ.ም/ በጥሩ ሁኔታ አጠናቅቆ ተግብሯል፡፡ እንዲሁም የ5ኛውን ስትረቴጅክ እቅድ ከ 2011 እስከ 2015 ዓ.ም ድረስ በመተግበር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡

6ተኛውን የስትራቴጅክ እቅድ (እ.ኤ.አ 2021-2025) ሲያዘጋጅ ከአማራ ክልል በተጨማሪ በመላው ኢትዮጵያ ልማታዊ ስራዎችን ለመከወን ያቀደበት እና ከ4 ፕሮግራሞች ወደ 5 ፕሮግራሞች ያደገበት ነው፡፡ እነርሱም የደን፣ አካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም፣የውሃ፣ ስነ-ንፅህና እና መስኖ ልማት ፕሮግራም፣የግብርና እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፕሮግራም፣የስርዓተ-ፆታ፣ አካል ጉዳተኝነት አካታችነት እና የወጣቶች ኢንተርፕራይዝ ፕሮግራም፣የምግብ እህል አስተዳደር እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራም ናቸው፡፡

አመልድ ኢትዮጵያ ተልዕኮውን ለማሳካት የሚከተላቸው ዋና ዋና የልማት አቅጣጫዎች

 • የአካባቢ ደህንነትን ማረጋገጥ እና ድሃ ቤተሰቦችን ኑሮ ለማሻሻል የተለያዩ የገቢ አማራጮችን ማስፋት ፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን ዘላቂ በመጠበቅ እና አጠቃቀምን ማሻሻል፣
 • የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን በማሻሻል የአካባቢ ጽዳትና የግል ንፅህና አጠባበቅን በማሳደግ ጤናማ ማህበረሰቦችን እና ንቁ የሥራ ኃይልን መፍጠር፣
 • የሰብል ምርታማነትን እና ምርትን ከፍ ለማድረግ መስኖ መሰረተ-ልማቶችን በመገንባት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣
 • የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን እና ልምዶችን በማስተዋወቅ አርሶ አደሮች ምርትንና ምርታማነትን በማሳደግ ዘላቂ የኑሮ መሻሻል እንዲያመጡ ማገዝ፣
 • መሬት ለሌላቸው እና ሥራ አጥ ለሆኑ ሴቶችና ወጣቶች አስተማማኝ የገቢ ምንጭ ለመፍጠር የሚያስችላቸውን የእርሻ እና እርሻ ያልሆኑ የኑሮ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
 • ከላይ በተጠቀሱት ሁሉም ልማቶች ስርዓተ- ጾታ ፣ ኤች.አይ.ቪ / ኤድስ ፣ አመጋገብ ፣ ወጣቶች ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስራዎችን ታሳቢ በማድርግ መፈፀም ናቸው፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያአስተዳደር መዋቅር፡-

አመልድ ኢትዮጵያ ጠቅላላ ጉባየተመሰረተው በተመሠረተበት ክልል ውስጥ ነው፡፡ ለአራት ዓመታት በጠቅላላ ጉባኤው የሚመረጠው ሁለተኛው ከፍተኛ የአስተዳደር አካል የዳይሬክተሮች ቦርድ ሲሆን በተራው ደግሞ ሥራ አስፈፃሚውን እና ምክትል ዳይሬክተሮችን ይመድባል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ የድርጅታዊ ስትራቴጂዎችን እና እቅዶችን አፈፃፀም በበላይነት በመቆጣጠር ለድርጅቱ አመራር አጠቃላይ መመሪያ ይሰጣል፡፡ ሥራ አስፈፃሚው ከድርጅቱ አስተዳደር ጋር በመመካከር የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆችን በተወዳዳሪነት መሠረት ይመድባል፡፡ ስራ አስፈፃሚው ተጠሪነቱ ለድርጅቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ነው፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ የአስተዳደር ኮሚቴ ከሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ከምክትል ዳይሬክተሮች ከፕሮግራም ዳይሬክተሮች ከፕሮግራም ሥራ አስኪያጆች ከአስተባባሪና ከአገልግሎት ሥራ አስኪያጆች የተውጣጣ ነው ፡፡ የድርጅቱ አስተዳደር የፕሮግራሞችን እና የፕሮጀክቶችን ትግበራ በበላይነት የሚቆጣጠር ሲሆን ሰራተኞችን ለተሻለ አፈፃፀም ያነሳሳል፡፡

የአመልድ ኢትዮጵያ ዋና ዋና ልማት ፕሮግራሞች፡-

 1. የደን፣ አካባቢ እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም፣የውሃ፣
 2. ስነ-ንፅህና እና መስኖ ልማት ፕሮግራም፣
 3. የግብርና እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፕሮግራም፣
 4. የስርዓተ-ፆታ፣ አካል ጉዳተኝነት አካታችነት እና የወጣቶች ኢንተርፕራይዝ ፕሮግራም፣
 5. የምግብ እህል አስተዳደር እና የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ፕሮግራም ናቸው፡፡

xmLD x!T×à xm¬ bjTÝ(

 • በ1989 ዓ.ም 21.77 የነበረው ዓመታዊ በጀቱ 1994 54.7 ሚሊዬን ብርደረሰ፤
 • በ1995/96 . ዓመታዊ በጀቱ 36.5 ሚሊዬን ብርነበር፤
 • በ2003 . ዓመታዊ በጀቱ 364.3 ሚሊዬን ብርወይም 21.2 ሚሊዬንዶላርነበር፡፡
 • በ2004 ዓ.ም ዓመታዊ በጀቱ 440.2 ሚሊዬን ብር ወይም 25.62 ሚሊዬን ዶላር ነበር፡፡
 • በ2005 ዓ.ም ዓመታዊ በጀቱ 509.2 ሚሊዬን ብር ወይም 29.63 ሚሊዬን ዶላር ደርሷል፡፡
 • በ2008 . ዓመታዊ በጀቱ 900 ሚሊዬን ብርበላይሲሆን 
 • 2009  .ደግሞ ዓመታዊ በጀቱ 1 ሊዬን ብርበላይሆኗል፡፡
 • በ2010 ዓ.ም ዓመታዊ በጀቱ 581.12 ሚሊዮን ብር ሲሆን፤
 • በ2011 ዓ.ም ደግሞ 1,184.62 ሚሊዮን ብር ነበር፡፡

 y¸NqúqSÆcW wrÄãC

 • b1995¼96 ዓ.ም y¸NqúqSÆcW wrÄãC B²T SMNT nbRÝÝ
 • b2003¼04 ዓ.ም b81 wrÄãC PéjKèCN b¥µÿD k3.5 ¸l!üN HZB b§Y t-”¸ xDRÙLÝÝ
 • b2004¼05 ዓ.ም 1.6 ¸l!üN HZB t-”¸ y¸ÃdRg# PéjKèC b64 wrÄãC bmµÿD §Y Yg¾l#ÝÝ
 • 1995¼96 . ለአመልድ የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች ቁጥር ሰባት ነበር፤
 • b2003¼04 ዓ.ምአመልድን የሚደግፉረጂድርጅቶች ቁጥር 26 ነበር፡፡
 • b2004¼05 ዓ.ም ደግሞÃHL yr©! DRJèc$ xmLDN dGfêLÝÝ
 • bx-”§Y k1983 ዓ.ም እስከ2005 ›.M lxmLD ygNzB DUF Ãdrg# r©! DRJèC bDM„ 44 ÂcWÝÝ 
 • ከ2008- 2009 ዓ.ም ድርስ አመልድ ከ30 በላይ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ጋር የልማት ስራዎችን ያከናውናል፡፡
 • በ2010 ዓ.ም 39 ፕሮጀክቶችን በማንቀሳቀስ በ68 ወረዳዎች የሚገኝ 1.5 ሚሊዮን ህዝብ ማልማት ተችሏል፡፡
 • እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በ53 ወረዳዎች 643.46 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ 1.45 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
 • በ2012 ዓ.ም አመልድ ኢትዮጵያ 1.4 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 31 የተቀናጁ ፕሮጀክቶችን (ሁለት አስቸኳይ እርዳታ ፕሮጀክቶችን) በአማራ ክልል 47 ወረዳዎች ተግባራዊ አድርጓል፡፡
 • በ2010 ዓ.ም 39 ፕሮጀክቶችን በማንቀሳቀስ በ68 ወረዳዎች የሚገኝ 1.5 ሚሊዮን ህዝብ ማልማት ተችሏል፡፡
 • እንዲሁም በ2011 ዓ.ም በ53 ወረዳዎች 643.46 ሚሊዮን ብር በጀት በመመደብ 1.45 ሚሊዮን ህዝብ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡
 • በ2012 ዓ.ም አመልድ ኢትዮጵያ 1.4 ሚሊዮን ሰዎችን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 31 የተቀናጁ ፕሮጀክቶችን (ሁለት አስቸኳይ እርዳታ ፕሮጀክቶችን) በአማራ ክልል 47 ወረዳዎች ተግባራዊ አድርጓል፡፡

  yPéjKT ¥StÆb¶Ã {¼b@èC

 • አመልድ ኢትዩጵያ በዞን ደረጃ 7 አና በወረዳ ደረጃ 27 የፕሮጀክት ማስተባበሪያ ጽ/ቤቶች አሉት፡፡

ysW hYL

 • በአሁኑ ወቅት (እ.ኤ.አ. በሚያዚያ 2021) የአመልድ ኢትዮጵያ ጠቅላላ ሠራተኞች 2138 (665 ሴት) ናቸው::

bxÆLnT y¸útFÆcW ytlÆ mDr÷C ኔትዎርኮች

አመልድኢትዮጵያ በኢትዮጵያ ውስጥ ተመስርተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የግንኙነት መድረኮች/መረቦች /Network Organizations/ አባል ሲሆን የአብዛኞቹም መስራች ነው፤ አባል የሆነባቸው የግንኙነት መድረኮችም የሚከተሉት ናቸው፤  

 • የክርስቲያን በጎ አድራጎትና ልማት ጥምረት /ኮንሰርቲዬም/ ማህበር፣
 • አመልድ የኢትዮጵያ ናይል ተፋሰስ የምክክር መድረክ፣
 • የዘላቂ መሬት አጠቃቀም መድረክ፣
 • በኢትዮጵያ ለድህነት ቅነሳ የተግባር ግንኙነት
 • የስነ ህዝብ፣ ጤናና አካባቢ ቅንጅት ኮንሰርቲዬም ወይም ማህበር
 • የስነ ህዝብ፣ ጤናና አካባቢ የምክክር መድረክ፣
 • የበርሃማነት መከላከል ማህበር እና
 • ኤች አይ ቪና ስነ ተዋልዶ፣ የምግብ ዋስትና፣ አካባቢ ጥበቃና ስርዓተ ጾታ ጉዳዮች ላይ አተኩረው የተመሰረቱና የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ክልላዊና አገር አቀፍ የምክክር መድረኮች አባል ነው፡

DRJt$ Ãg¾cW xlM xqF xgR xqF >L¥èC

 • በአለም አቀፍ ደረጃ ያገኛቸው ሽልማቶች
  • yxGé xK>N
  • በ2008/2009 ዓ.ም ድርጅቱ በሳየው የላቀ የልማት ስራ ከአውሮፓ የጥራት ምርምር ማዕከል የዋንጫና የምስክር ወረቀተተሸላሚሆኗል፡፡
 • በአገር አቀፍ ደረጃ ያገኛቸው ሽልማቶች
  • 1999¼2000ዓ.ም በተፈጥሮ ሃብት ልማት ላሳየው የላቀ አፈፃፀም የመጀመሪያ ደረጃ ብሄራዊ የአረንጓዴ ሽልማት
  • የሚሊኒየም የልማት ግብ የግልና የአካባቢ ንፅህና ተሸላሚ
  • በ2008 ዓ.ም አራተኛው የኢትዩጵያ ጥራት ሽልማት ውድድር ላይ ድርጅቱ በሳየው የላቀ የልማት ስራ የዋንጫና የምስክር ወረቀተ ተሸላሚ ሆኗል፡፡


Last Updated (Thursday, 06 April 2023 08:18)