Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Home ስለ አመልድ ኢትዮጵያ የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

                   የዋና ዳይሬክተሩ መልዕክት

አመልድ ኢትዮጵያ ስትራቴጅያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የህዝቡንና የመንግስትን የልማት ክፍተቶች በመሙላት ከተቋቋመበት ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ትርጉም ያለው የልማት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

 

          dr.Amharic message

 

አመልድ ኢትዮጵያ አምስት ዋና ዋ ናየልማት ፕሮግራሞች አሉት፡፡ 

እነዚህም፡

  1የአካባቢ፣ ደን ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥ ፕሮግራም

  2.ንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት፣ሃይጅን፣ሳኒቴሽን መስኖና መሰረተ ልማት ፕሮግራም፣

  3. ግብርና፣ ስርዓተ ምግብና አደጋ ስጋት ስራ አመራር፣

  4. የስርዓተ ጾታ፣ አካል ጉዳተኝት አካታችነትና የወጣቶች ስራ ዕድል ፈጠራ ፕሮግራም፣

  5. የእህል አስተዳደርና የአደጋ ምላሽ ሰጭ ፕሮግራም ናቸው፡፡

ድርጅቱ የደን ልማት ስራዎችን በማጠናከር፣ ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶ አደሩ  በማቅረብ የንጹህ መጠጥ ውሃ በማድረስ፣ የግልና የአካባቢ  ጽህናን በመጠበቅና ትራኮማን በመከላከል፣ አነስተኛ  የመስኖ አውታሮችን በመዘርጋት፣ ስርዓተ-ምግብን በማሻሻልና መቀንጨርን በመከላከል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡    

በአሁኑ ሰዓት ድርጅቱ ከለጋሽ ድርጅቶች በሚያገኘው ሃብት  በከፋ ድህነት ውስጥ የሚኖሩ ወገኖቻችንን ኑሮ ለመለወጥ እየሰራ ሲሆን መንግስታዊ ተቋማት፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችና አጋሮች ለተሻለ የልማት ስራ በጋራ ለመለወጥ ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 


ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
ምርጥ ተሞክሮ