የተለየዩ የአቅም ግንባታ ስልጣናዎች ለአመልድ ሰራተኞች ተሰጡ

በታደሰ ዘበአማን

                                        capacity building

ቁጥራቸው ከ40 ለሚበልጡ የአመልድ የፕሮጀክት ማኔጀሮች፣ ከፍተኛ ባለሙያዎችና የፕሮጀክት የክትትልና ግምገማ ባለሙያዎች ለአምስት ቀናት የቆየ በፕሮጀክት ፕሮፖዛል ዝግጅትና በሪፖርት አፃፃፍ ላይ ያተኮረ ስልጠና በአቶ ደበበ ታዬ በምግብ ለተራቡ ኢትዮጵያ ድርጅት የአመልድ  የአቅም ግንባታ አማካሪ ከጥር 19-22/ 2007 ዓ.ም በአዲስ አምባ ሆቴል ተሰጠ፡፡

በስልጠናውም ወቅት የፕሮጀክት ፕሮፖዛልና የሪፖርት አፃፃፍን በተመለከተ ንድፈ ሃሳቦችና ተግባራዊ ልምምዶች አንዲሁም ከአሁን በፊት በድርጅቱ የተሰሩ ፕሮፖዛሎችንና ሪፖርቶችን ሰልጣኞች በመገምገም የፅሁፎችን ህጸጾች እንዲለዩ በማድረግ የተሻለ እውቀት እንዲጨብጡ ጥረት ተደርጓል፡፡

እንዲሁም በ24/05/07 ዓ.ም. ደግሞ 35 ለሚሆኑ የፕሮግራም ዳይሬክተሮች፣ ማናጀሮችና የፕሮጀክት ማናጀሮችና የኮሙኒኬሽንና አይቲ ክፍል ባለሙያዎች በአድቫንስድ ወርድ፣ ኤክስኤልና ፓወር ፖይንት አፕሊኬሽኖች ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን ስልጠና ከምግባ ለተራቡ ኢትዮጵያ ድርጅት በመጡ አቶ ዳንኤል ገበየሁ በተባሉ የድርጅቱ የአደጋና ሪስክ ዳይሬከተር ስልጠና ተሰጥቷል፡፡

                              capacity building1

ሁለቱም ስልጠና ላይ የተሳተፉ ሰልጣኞች ስልጠናዎቹ ቲወረቲካል ብቻ ስላልሆኑና በተግባራዊ ልምምድ የታገዙ ስለነበሩ ከአሁን በፊት የነበሩባቸውን የአቅም ክፍተቶች የሚደፍኑ እንደሆኑ ገልፀዋል፡፡

Copyright © 2012 ORDA Ethiopia.
All Rights Reserved.