ኤ ግሊመር ኦፍ ሆፕ ድርጅት የስራ ሃላፊዎችና ረጅ ባለሃብቶች የፕሮጀክት ቦታዎችን ጎበኙ

በታደሰ ዘበአማን

                                               Gilmer

ግሊመር ኦፍ ሆፕ ድርጅት በአማራ ክልል የመጠጥ ውሃ፣ ጤናና ትምህርት ልማት እንዲስፋፋ ከበርካታ አመታት ጀምሮ ሲረዳ እንደቆየ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ ጥረቱን ለማስቀጠል ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት አመታት የሚቆይ ፕሮጀክት በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በሚገኙ 10 ቀበሌዎች ዉስጥ ለመተግበር ዝግጅቱን እንደጨረሰ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዶና ባርበር ገልፀዋል፡፡ ለ2015 የበጀት አመትም 28 ሚሊዮን ብር መመደቡ ታውቋል፡፡

ወ/ሮ ዶና ይህን የገለፁት እ.አ.አ ከጥር 18-20/ 2007 በቆየ ጉብኝት በጎንደር ዙሪያ በሚገኙ ፕሮጀክቱ ወደፊት በሚፈፀምባቸው ሶስት ቀበሌዎችና ከአሁን በፊት ድርጅቱ የተለያዩ ስራዎችን እንዲሰሩ በደገፈበት በቡርቧክስ ቀበሌ በተገኙበት ወቅት ነበር፡፡

                                 Gilmer2

የፕሮጀክቱ ዋና ዋና ስራዎች መካከል የትምህርት ተቋማት ፣ የጤና ጣቢያ ፣ የንፁሕ መጠጥ ውሃ ተቋማት ግንባታና ለመስኖና ለእንስሳት ሃብት ልማት ስራ የሚውል ብድር አገልግሎት ይገኙበታል፡፡ የጤና ተቋማትና የትምህርት ቤቶችን ግንባታዎችን በአልማ፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታዎችን ደግሞ በአመልድ እንዲሁም የብድር አገልግሎቱ ደግሞ በአብቁተ የሚሰራ ይሆናል፡፡

ሚስ ዶና በርበር እና በእርሳቸዉ የሚመራው ለድርጅታቸው የገንዘብ ድጋፍ ለሚያደርጉ ባለሃብቶችና የድርጅታቸውን የኢትዮጵያ ቢሮ ሃላፊዎችንና ባለሙያዎችን ያካተተ የልኡካን ቡድንን የአመልድ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አምላኩ አስረስና የአልማ ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ብስራት ጋሻው ጠና ጎንደር አዉሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀበቀበል አድርገውላቸዋል፡፡

                                 Gilmer1

ቡድኑ በሶስት ቀናት ቆይታው በተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኙ የአዲሱ ፕሮጀክት የማሻሻያ ስራ የሚሰራላቸውንና በጣም የተጎሳቆሉ ጤና ጣቢያዎችን፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አንዲሁም የመስኖ ቦታዎችን፣ ተጠቃሚ ሴቶችን ቤታቸው ድረስ በመሄድ ጎብኝተዋል እንዲሁመ ከአሁን በፊት የተሰሩ የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን ጎብኝተዋል፡፡ በሁሉም ቀበሌዎች ማለት ይቻላል ለቡድኑ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

                              Gilmer3

ለቡድኑ ክብርም ሲባል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በተገኙበት በጎሃ ሆቴል በክልሉ መንግስት ስም የራት ግብዣ ተደርጎላቸዋል፡፡

እንዳጠቃላይ ጉብኝቱ የታለመለትን አላማ እንደመታ መገንዘብ ተችሏል፡፡

Copyright © 2012 ORDA Ethiopia.
All Rights Reserved.