Print

አመልድ ከኢፋድ ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ የገነባቸው 16 መስኖዎች ተመረቁ

በታደሰ ዘበአማን

                  ss1

አመልድ ከኢፋድ የአሳታፊ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት ጋር በገባው ስምምነት መሰረት ሊገነባ ከተረከባቸው 16 መስኖዎች መካከል 4 ከፌደራል የግብርና ሚኒስትር ከፌደራል የኢፋድ አሳታፊ አስተኛ መስኖ ልማት ፕሮጀክት ሃላፊ፣ የአመልድ ዳይሬክተር ሌሎችም የክልልና የዞን እንዲሁም የወረዳ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ግንቦት 29 እና 30 2007 . ተመረቁ፡፡ ሁሉም ግንባታዎች የተጠናቀቁ ቢሆንም በሁለቱ ቀናት ፕሮግራም የተመረቁት ግን ሶስቱ ብቻ ናቸው፡፡ የተመረቁትም መስኖዎች /ጎንደር ዞን የሚገኘው የገልዳ አነስተኛ መስኖ፣ አዊ /አስ/ዞን ዳንግላ ወረዳ የሚገኘው የጊዛኒ መስኖ፣ አዊ /አስ/ዞን ባንጃ ወረዳ የሚገኘው የቡችክሲ መስኖና በምዕ/ጎጃም ዞን ወምበርማ ወረዳ የሚገኘው የካሉ መስኖ ልማት አውታሮች ናቸው፡፡ 

በምረቃው ወቅት አመልድ 2014 ገንብቶ ለጥቅም ካዋላቸው የመስኖ አውታሮች መካከል 8 2014 ተጀምረው በዛው አመት የተጠናቀቁ ሲሆኑ ቀሪዎቹ 8 ደግሞ በዲዛይንና በግንባታ ጥራት ምክንያት እንደ አዲስ እንዲሰሩ የተወሰኑና 2013 የተሸጋገሩ መሆናቸው ተገልጧል፡፡ የዘንድሮውን ግንባታ ለየት የሚያደርገው አብዛኞቹ ግንባታዎችን ለማጠናቀቅ ከሶስት ወር እስከ 7 ወራት ብቻ የወሰዱ መሆኑ ነው፡፡ ሌላው ለሌቹ ተመሳሳይ ግንባታዎች አስተማሪ ሆኖ የተገኘው ደግሞ በተለምዶ እስካሁን የአ/አደር ማሳ ሰብል ካልተነሳ በሚል ህዳር ወር ላይ ግንባታዎች አይሰሩም ነበር፡፡ 2014 ግንባታዎች ግን አመልድ፣ ከክልል እስከ ቀበሌ ያለው የመንግስት መዋቅር ባደረጉት ርብርብ አርሶ አደሩ በግንባታዎቹ ላይ እንዲያምንባቸው በመደረጉ ለመታጨድ አስር ቀን ብቻ የቀረውን እህል እንኳን ሳይቀር አጭዶ ማሳውን ለግንባታ እንዲውል በመፍቀዱ ምክንያት መስኖዎቹ ህዳር ታህሳስ ወራትም ሊገነቡ መቻላቻውን አቶ ጉግሳ መሸሻ የአመልድ የውሃ ልማት ዳይሬክተር ገልፀዋል፡፡


                       ss5

የአብክመ ግብርና ቢሮ ሃላፊ የሆኑት / ተሾመ ዋለ በበኩላቸው የእነዚህ መስኖዎች ግንባታ በመስኖ ግንባታ ላይ ህዳሴ ማምጣታቸውን ገልፀዋል፡፡ የፌደራል ኢፋድ የአሳታፊ መስኖ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ጀማል አልይ በበኩላቸው በአመልድ 2014 እጅግ በጣም ፈጣን ሊባል የሚችል የፕሮጀክት አፈፃፀም ምክንያት ከኢፋድ ለአሳታፊ መስኖ ልማት በሃገር አቀፍ ደረጃ ሊቋረጥ የነበረው የበጀት ለቀጣይ አመታትም እንዲቀጥል ሆኗል፡፡ ለዚህም ውጤት አቶ ጀማል አመልድንና የክልሉን መንግስት አመስግነዋል፡፡ አቶ ጀማል አያይዘውም ድርጅታቸው ኢፋድ ይህን የአመልድ ምርጥ የአፈፃፀም ተሞክሮ ለመቀመርና ለሌሎች ክልሎች ለማስተላለፍ በቅርብ ጊዜ የተለያየ ስራዎችን እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡ 

የመስኖዎቹ ተጠቃሚ የሆኑ አርሶ አደሮች በበኩላቸው በኢፋድ የገንዘብ ድጋፍ በአመልድ በተሰራላቸው የመስኖ አውታር በመጠቀም በአመት ከሁለት በላይ ጊዜ የማምረት አቅም እንደፈጠረላቸውና ወደፊትም እንዚህን መስኖዎች በመጠቀም ጠንክረው በመስራት ህይወታቸውን እንደሚለውጡ ቃል ገብተዋል፡፡ 
በምረቃው ማጠናቀቂያ ላይ ደግሞ በግንባታው ስራ ላይ ግንባር ቀደም ተዋናይ የነበሩ 28 የአመልድ መሃንዲሶች፣ ፎረርማኖች፣ ሾፌሮች፣ የመጋዝን ሰራተኞችና 4 የአማራ ዲዛይንና ቁጥጥር ስራዎች መሃንዲሶችና አንዲት የአማራ ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ መሃንዲስ በአመልድ ተሸልመዋል፡፡


                       ss4