Print

የአመልድ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት የአመልድን ፕሮጀክቶች ጎበኙ

በታደሰ ዘበአማን

                           board0

የአመልድ ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እ.ኤ.አ ከጥር 1-4 2015 ባሉት አራት ቀናት ውስጥ በመስክ በመገኘት የተለያዩ የአመልድ ፕሮጀክቶችን ጎበኙ፡፡ የቦርድ አባላት የመስክ ጉብኝቱን ያደረጉት በሁለት ቡድን ተከፍለው ሲሆን አንደኛው ቡድን በምዕራብ አማራ ሁለተኛው ቡድን ደግሞ በምስራቅ አማራ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል፡፡

በምዕራብ አማራ ጉብኝት ያደረጉት የቦርድ አባላት ወ/ሮ ገነት ገ/እግዚአብሄር( የቦርዱ ምክትል ሰብሳቢ)፣ ክብርት ወ/ሮ ሽታየ ምናለና ዶ/ር አምላኩ አስረስ (የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተርና የቦርዱ አባል) ሲሆኑ በምስራቅ አማራው ቡድን ደግሞ አቶ ጌታቸው ጀንበሬና ዶ/ር ፀሐይ ጀምበር ይገኙበታል፡፡ የምዕራብ አማራው ቡድን ጉብኝት ያደረገው በአዊ ዞን ሶስት ወረዳዎችና በደ/ጎንደር ዞን ደግሞ በሶስት ወረዳዎች በድምሩ በስድስት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ነው፡፡ በምስራቅ አማራ ደግሞ በሰሜን ሸዋና በደቡብ ወሎ በሚገኙ አራት ወረዳዎች ናቸው፡፡

                           board

የጉብኝቱ ዓላማዎችም የአመልድን ስራዎች ለቦርዱ አባላት ለማሳየት፣ የሠራተኛውን ተነሳሽነት ለመጨመርና የቦርዱ አባላት ለፕሮጀክቶች ያላቸውን ግንዛቤ በማሳደግ በመስክ በመገኘት ስራዎችን የመደገፍ ልምዳቸውን ለማሳደግ ናቸው፡፡ ጉብኝቱ የታለመልትን አላማ ያሳካ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

board12board3

እንዲሁም ጉብኝቱም በጣም ጠቃሚ የሆኑ ልምዶች የተገኙበት እና ለወደፊቱም መቀጠል ያለበት ተግባር ነው፡፡