አመልድ የጀመራቸውን የለውጥ እንቅስቃሴዎች አጠናክሮ ከመቀጠል ባሻገር የትራንስፎርሜሽን እቅድ ሊኖረው እንደሚገባ  ተጠቆመ

በታደሰ ዘበአማን

                            leade4rship

የአመልድ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አምላኩ አስረስ አመልድ የጀመራቸውን የለዉጥ እንቅሰቃሴዎች አጠናክሮ ከመቀጠል ባሻገር የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ሊኖረው እንደሚገባ አሳሰቡ፡፡

ዳይሬክተሩ ይህን የተናገሩት ከህዳር 7-9 /2007 በአመልድ ዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደውና ለአመልድ ማኔጅመንት አባላት፣ ለፕሮጀክት ማኔጀሮችና አስተባባሪዎች፣ ለማስተባበሪያ ጽ/ቤት አስተባባሪዎች እና ለአመልድ ዋናው መስሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሙያዎች በተዘጋጀው የለዉጥ ስራ አመራር ስልጠና ማጠናቀቂያ ላይ በተካሄደው ውይይት ወቅት ነው፡፡

leadership 1leadership

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) በተፈጥሮ ሃብት፣ በውሃ፣ በምግብ ዋስትናና የግብርና ልማት እንዲሁም በወጣቶችና ስርዓተ-ጾታና ዘርፎች በክልሉ ውስጥ መጠነ-ሰፊ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በተለይ በአሁኑ ሰዓት የሚከናወኑ የልማት ስራዎችን ወደ ከፍታ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ስልጠናው የተዘጋጀውም ይህን ለውጥ እንዲያግዝ በሚል አላማ ነው፡፡

ስልጠናውን የሰጠው ከዶቭ ስራ አመራር የማማከር፣ ስልጠናና ምርምር .የተ. የግል ኩባንያ በመጡና የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ባለሙያ በአቶ ሰማ መኮነን እና የFH አቅም ግንባታ አማካሪ የሆኑት አቶ ደበበ ታየ ሲሆኑ በስልጠናው የለውጥ አመራር፣ የልማት ኮሙኒኬሽን፣ ትራንስፎርሜሸናል አመራር እና ዉጤታማ የልማት ቡድን አገነባብ የሚሉትን ያካተተ ነበር፡፡

  leadership 2leadership 3

ስልጠናው መገባደጃ ላይም የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር እየመሩት ስልጠናው አመልድ ከጀመራቸው የለውጥ እንቅስቃሴዎች አንፃር ምን ፋይዳ ነበረው በሚለዉ ርዕስ ላይ ሰልጣኞች ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም ላይ አመልድ በእድገት ላይ ቢሆንም አሁንም ግን ሊሻገራቸው የሚገባቸው እጥረቶች እንዳሉበት ታምኖ ከ2014 የስድስት ወራት የስራ ግምገማን ተከትሎ በለውጥ ውስጥ እንደገባ ተረጋግጧል፡፡ ስልጠናውም አመልድ እያጋጠሙት ያሉትን ችግሮች ለመፍታት እየወሰዳቸው ያሉት የመፍትሄ ርምጃዎች ትክክለኛና ሳይንሳዊ መሆናቸውን እንዲረዱ ያስቻላቸው መሆኑን የስልጠናው ተሳታፊዎች በውይይቱ ወቅት አረጋግጠዋል፡፡

በውይይቱ የተነሳው ሌላው ነገር ደግሞ አመልድ ከጀመራቸው አዳጊና ሂደታዊ ለውጦች በተጨማሪ በመጪው ጊዜ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ድርጅታዊ፣ ክልላዊ፣ ሃገራዊና አለማዊ ሁኔታዎች አንጻር የተቃኘ፣ ድርጅቱም ከ10ና ከ20 አመታት በኃላ ሊደርስበት የሚገባውን ደረጃና በረጅም ጊዜ ድርጅቱ ሊገጥሙት የሚችሉትን ችግሮች ለመፍታት የሚያስችል ተቋማዊ የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማዘጋጀት እንዳለበት ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ 

Copyright © 2012 ORDA Ethiopia.
All Rights Reserved.