Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ አገልግሎቶች ፋይናንስና ግራንት መምሪያ

የፋይናንስ አመራር

አመልድ ውጤታማ የፋይናንስ ስርዓት በመዘርጋት ከተለያዩ ምንጮች የሚያሰባስበውን ገንዘብና ሌሎች ሀብቶች ሃላፊነትና ተጠያቂነት በተመላበት ሁኔታ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡ ይኸው ስርዓትም ከግዥና ከሰው ሃይል አመራሩ ጋር የተጣጣመ ተደርጓል፡፡ የፋይናንስ አመራሩ ለአሰራር ቀላልና ምቹ ሲሆን በየደረጃው ሙሉ በሙሉም ሆነ በተለዬ ሁኔታ ተወክለው በሚገኙ ሃላፊዎች በተገቢ ሁኔታ ስራ ላይ እየዋለ ነው፡፡ 

ከዚህ ባሻገር የፋይናንስ ስርዓቱ በኮምፒውተር የተደራጀ ሲሆን በውስን አካባቢ በተዘረጋ ኔትውርክ /Local Area Network  (LAN)/ ታግዞ ስራ ላይ ውሏል፡፡ ይኸው አደረጃጀት በድርጅቱ ውስጥ ለፋይናንሱ አመራርና አስተዳደር ሃላፊነት የተጣለባቸው ሃላፊዎችና ሰራተኞች በያሉበት ወይም በየቢሯቸው የተዘረጋውን ስርዓት በቀላሉ እንዲያገኙትና ስራዎቻቸውን እንዲፈጽሙ የሚያስችል ሁኔታ ፈጥሯል፡፡ የድርጅቱን የሂሳብ መዝገብ በቋሚነት የሚመረምሩ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያገኙ እውቅ ኦዲተሮች በተዘረጋው ስርዓት የማስፈጸም አቅም/ችሎታና ብቃት ምንጊዜም ደስተኛ ናቸው፡፡  የተዘረጋው ስርዓት ብቁነት በባለድርሻ አካላትና በጋሽ ድርጅቶቹም በኩል እውቅናን ተጎናጽፏል፡፡ በተጨማሪም የአመልድ የፋይናንስ ሪፖርቶች ለሚመለከተቻው ሁሉም ባለድርሻ አካላት እንዲሰራጩ ይደረጋሉ፡፡

በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ቁጥር 621/2001 ዓ.ም አንቀጽ 68 መሰረት በየአመቱ አመልድ የሂሳብ መዝገቦችን የሚመረምር የውጭ የሂሳብ ምርመራ የሚያካሂድ ድርጅት ይቀጥራል፤ የሂሳብ ምርመራ ውጤት ሪፖርትም ለአመልድ አመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ እንዲቀርብ ያደርጋል፡፡

ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today21
Week349
All74926

Currently are 10 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?