Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

ዋና ገፅ ዜና የቅርብ ዜናዎች ወጣቶችን በተለያዩ የስራ መስኮች ለማሰማራት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

               ወጣቶችን በተለያዩ የስራ መስኮች ለማሰማራት የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

             RESET SAVE Logo

በአማራ እና የሶማሌ ክልሎች ወጣቶችን በተለያዩ የስራ መስኮች ለማሰማራት የሚያስችል አዲስ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ፡፡ ይህ ፕሮጀክት 15 እስከ 29 ዓመት ዕድሜ ላላቸው ስራ አጥ ወጣት ወንዶች እና ሴቶች ያለአድሎ በተመጣጣኝ ክፍያ ዘላቂና የተረጋጋ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ጥረት ያደርጋል፡፡

ፕሮጀክቱ 4,500 ለሚሆኑ በድህነት ውስጥ ለሚገኙና እና ለስራ አጥነት የተጋለጡ ወጣት ልጃገረዶች/ ሴቶች እና ወንዶች የገቢ መጠናቸውን ለማሻሻል፣ የስራ አጥነትን ቁጥር ለመቀነስ እንዲሁም የስራ ላይ ቆይታን/ቶሎ የመልቀቅ ችግሮችን ለመቅረፍ ያለመ ነው፡፡

አቶ አበበ ተቀባ የዋግኸምራ የዞን ምክትል አስተዳዳሪ አውደ ጥናቱን ሲከፍቱ

               RESET

የወጣቶች አደጋ ተጋላጭነት መቀነስ ፕሮጀክት "RESET Plus" 2.57 ሚሊዮን ዩሮ ወይንም (82.3 ሚሊዮን ብር ) የአውሮፓ ኅብረት የገንዘብ ድጋፍ በተመረጡ 4 ወረዳዎች (ሰቆጣ ዙሪያ፣ ዝቋላ፣ ጋዝጊብላና ደሃና እኤአ ከሚያዝያ 2018 ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2021 የሚተገበር ነው፡፡

አመልድ ፕሮጀክቱን በጋዝጊብላና ደሃና ወረዳዎች ውስጥ ተግባራዊ የሚያደርግ ሲሆን የኢትዮጵያ ሕፃናት አድን ድርጅት /Save the Children/ ደግሞ በሰቆጣ ዙሪያና ዝቋላ ወረዳዎች ለእያንዳንዳቸው በተመደበ 1.12 ሚሊዮን ዩሮ በጀት ይፈጽማሉ፡፡

የወጣቶች ዝቅተኛ የስራ ክህሎት መኖር፣ የመሬት አልባነት፣ በገጠር ዝቅተኛ የሥራ ስምሪት እና ኢኮኖሚያዊ ዕድሎች አለመኖር፣ ባህላዊ፣ ስነ-ባህሪ እና ለስራ የሚስተዋለው የተዛባ አመለካከት ለስራ አጥነት ችግሮች እንደ ምክንያት ይነሳሉ፡፡. ስለሆነም ፕሮጀክቱ የወጣቶችን አቅምና ክህሎት በመገንባት ወደ ተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለማሸጋገር ፕሮጀክቱ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል::

                RESET1

የፕሮጀክቱ መክፈቻ አውደ-ጥናት ጥቅምት 25/ 2011 . በሰቆጣ ከተማ ሲካሄድ አመልድ፣ የኢትዮጵያ ሕፃናት አድን ድርጅትና /Save the Children/ ኦክስፋም ጂቢ /Oxfam GB/ ከባለድርሻ አካላት ማለትም የዋግኸምራ ዞን አስተዳደር፣ የንግዱ ማሕበረሰብ፣ የወረዳ ጥቃቅንና አነስተኛ፣ ወጣቶችና ስፖርት፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት እና ሌሎች ተጠሪዎች ፕሮጀክቱን በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን ቃል ገብተዋል፡፡

አቶ አበበ ተቀባ የዋግኸምራ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ "ይህ ፕሮጀክት በአካባቢው ላሉት ሥራ የሌላቸው ወጣቶች ጥሩ አጋጣሚ በመሆኑ የፕሮጀክቱን ግቦች ለማሳካት ኃላፊነት አለብን " ብለዋል፡፡ በመጨረሻም ምክትል አስተዳዳሪው ፕሮጀክቱን ፍሬያማ በማድረግ አርአያ የሚሆኑትን ወደ ሌሎች አካባቢዎች ማስፋት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Last Updated (Wednesday, 07 November 2018 11:32)

 
ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookTwitter
የጎብኝዎች ብዛት
Today18
Week176
All75111

Currently are 20 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?