Joomla TemplatesBest Web HostingBest Joomla Hosting

Content on this page requires a newer version of Adobe Flash Player.

Get Adobe Flash player

ዋና ገፅ ዜና የቅርብ ዜናዎች አመልድ ከ4 ሚሊዮን በላይ ችግኝ እየተከለ መሆኑን አስታወቀ

                        አመልድ 4 ሚሊዮን በላይ ችግኝ እየተከለ መሆኑን አስታወቀ

                   greening2017

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) 1 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት 4 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአገር በቀልና የውጭ ዝርያ ያላቸውን ችግኞች በግሪኒንግ ፕሮግራም በሶስት ወረዳዎች ተከላ እያካሄደ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በዘንድሮው 2009 . በአሳታፊ የማኅበረሰብ አቀፍ ማረንጎድ (ግሪኒንግ) በተሰኘ ፕሮግራሙ በጎንደር ዙሪያ፣ ግዳንና ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች በተጋጋጡና ለምነታቸውን ባጡ አካባቢዎች በየዓመቱ እየተከ ሲሆን የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ግብርና ልማት ጽህፈት ቤት ባለሙያዎችና ተከላ የሚካሄድባቸው የቀበሌ ነዋሪዎችም በችግኝ ተከላው ተሳትፈዋል፡፡

የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አዝማች ብርሃኑ በሱርሳርዋ ቀበሌ የተከላ ፕሮግራም ሲገልጹ አመልድ የወረዳችን የተፈጥሮ ሃብት መልሶ እንዲያገግም በማድረግ ሰፊ ርብርብ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ዋና አስተዳዳሪው ድርጅቱ በሚሰራው ስራ ዛሬ የተራቆቱ ተራሮች አረንጓዴያማ ገጽታቸውን ጠብቀው ምርትና ምርታማነት እንዲጎለብት ሰፊ ሚና እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል፡፡

በሱርሳርዋ ቀበሌ መደቢት ጎጥ ችግኝ በመትከል ላይ ያገኘናቸው / መቅደስ እያዩ ሲናገሩ "ችግኝ በመትከላችን አፈራችን ተሟጦ እንዳይሄድ ከማድረጋችን ባሻገር ችግኝ ስንተክል የሚከፈለን ተመጣጣኝ ክፍያ የእለት ኑሮችንን ለመደገፍ ረድቶናል፡፡" ብለዋል፡፡

                   greening12017

የአመልድ የአካባቢና ደን ልማት ፕሮግራም ማኔጀር አቶ ጌታቸው አላምራው በዚህ ዓመት በአሳታፊ የማኅበረሰብ አቀፍ ደን ልማት ከመንግስት ጋር በድጋፍ 34 ሚሊዮን በላይ ችግኝ የተፈላ መሆኑንና በክልሉ ውስጥ በሚተገበሩ ፕሮጀክቶች አማካኝነት እየተተከለ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ ባለፉት ዓመታት 667 ሚሊዮን ችግኝ 1 መቶ 17 ሺህ ሄክታር በላይ ማልማት የቻለ ሲሆን በማረንጎድ (Greening) ፕሮግራም እንዲሁ 48.9 ሚሊዮን የዛፍ ችግኝ 17 ሺህ 260 ሄክታር ተሸፍኗል፡፡ ከዚህ ውስጥ ለጥቅም የደረሰ 14 ሺህ ሄክታር ደን ለመንግስትና ለህብረተሰቡ ማስረከቡን የድርጅቱ የኮሙኒኬሽንና አይቲ መምሪያ አስታውቋል፡፡

Last Updated (Tuesday, 25 July 2017 06:46)

 

 

የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ) ለክልሉና መላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን ለ2011 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ እያለ፡- 
---------------------------------------------------------------

         newyear
በክልላችን ስትራቴጅያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የአጭርና የረጅም ጊዜ ፕሮግራሞችንና ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ የመንግስትንና የህዝቡን የልማት ክፍተቶች በመሙላት ትርጉም ያለው የልማት ስራ እያከናወነ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ በአካባቢና ደን ልማት፣ የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ቴክኖሎጅዎችንና አሰራሮችን እንዲሁም የመስኖ ልማት አውታሮችን በመዘርጋት ጉልህ አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮችን በማላመድ፣ የገበያ ትስስር በመፍጠር፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት የክልሉን ልማት እየደገፈ ይገኛል፡፡

አመልድ የተሻሻሉ የሰብልና የእንስሳት ዝርያዎችን በአርሶ አደሩ ቀየ በማድረስ፣ የእናቶችና የህጻናት ስርዓተ ምግብ እንዲሻሻል፣ ስራ የሌላቸው ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር እንዲሁም ሴቶችና የአካል ጉዳተኞች

የኢኮኖሚው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

ድርጅቱ በሚያከናውናቸው የልማት ስኬቶች የውጭና የአገር ውስጥ ሽልማቶችን ያገኘ ሲሆን ከምንጊዜውም በተሻለ የልማት ስራዎችን በጋራ ለመስራት ለዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ድርጅቶች ጥሪውን ያቀርባል፡፡

አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅርና የብልጽግና እንዲሆንላችሁ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡ 
የአማራ መልሶ መቋቋምና ልማት ድርጅት (አመልድ)
--------------------------------------------------------
HAPPY ETHIOPIAN NEW YEAR- 2011 E.C.

 

 

We have got awarded "THE AMERICAN BIZZ 2017" prize for our outperforming accomplishments in program (Business) Excellence


ORDA’s Executive Director Acceptance Speech 


ORDA awarded globally the ESQR’s Quality Choice Prize 2016!

       

Organization for Rehabilitation & Development in Amhara (ORDA) is awarded 1st level trophy in the fourth Ethiopian Quality Award (EQA)

      

ቋንቋ
ሶሻል ሚዲያ
FacebookMySpaceTwitterGoogle Bookmarks
የጎብኝዎች ብዛት
Today0
Week51
All65121

Currently are 8 guests online


ምርጫ
ስለ ድረ-ገፅ ያለዎት አስተያየት ?